Lemlem Mekuant
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lemlem Mekuant, Health/Beauty, Dubai.
28/09/2025
መሰብ
07/10/2024
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?
***
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡
የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።
እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ወስደዋል።
በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።
አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።
በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፣
በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል።
በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፤
አምባሳደር ታዬ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል።
27/09/2024
ለምን አስለምደውን...?
17/07/2024
ህወሓት...
ህወሓት በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት በማያውቅ ፈተና ውስጥ እንዳለ አስታወቀ። ህወሓት የከፍተኛ አመራሮቹ ስብሰባ ካጠናቀቀ በኃላ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ ቡድናዊነት፣ ፀረ ዴሞክራሲ አመለካከቶች እና ህዝበኝነት ፈተናዎቹ እንደሆኑ አመልክቷል። አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው የህወሓት አመራሮች በክፍፍል ላይ መሆናቸው የሚያነሱ ሲሆን ይህም ለህዝቡ ተጨማሪ ችግር እንዳያስከትል ይሰጋሉ።
ከ 1,000 በላይ የህወሓት የተለያየ እርከን አመራሮች የተሳተፉበት እና ለ11 ቀናት “ብሄራዊ ህልውናችን ማረጋገጥ፣ ቀዳሚ ተግባራችን ነው” በሚል መሪ ሐሳብ ተደረገ ከተባለው ስብሰባ በኃላ፥ ትላንት መግለጫ ያወጣው ህወሓት ቡድናዊነት፣ ፀረ ዴሞክራሲ አመለካከቶች፣ ጎጠኝነት እና ህዝበኝነት ፈተናዎቹ ሆነው እንዳለ አመልክቷል። ህወሓት እንዳለው በ50 ዓመት ታሪኩ እንደ የአሁኑ ዓይነት ፈተና ገጥሞት እንደማያውቅ የሚያምን ሲሆን እነዚህ ፈተናዎች ፓርቲው በሚገባው ደረጃ እንዳይንቀሳቀስ ያደረጉ እና ወደ መፍረስ አደጋም ሲመሩ የነበሩ መሆናቸው አውስቷል።
በህወሓት መግለጫ አሁን ላይ በፓርቲው ውስጥ እየተደረገ ያለው ትግል በኪራይ ሰብሳቢነት እና ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መካከል ነው በማለት የሚያነሳ ሲሆን፥ ህወሓት ለማዳን ደግሞ ትግል እናደርጋለን ይላል። ከፌደራል መንግስቱ ጋር ሁለት ዓመት ለቆየ እና ለበርካቶች ሞት፣ ጉዳት፣ ስደት እና መፈናቀል ምክንያት በሆነ ጦርነት የቆየው፥ ቀጥሎም በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የተመለሰው ህወሓት፥ በሰላም ስምምነቱ የእስካሁን አፈፃፀም ጥሩ ጅማሮዎች ቢኖሩም የውሉ ይዘት በሙሉእነት በመተግበር፣ እንዲሁም በተያዘለት የግዜ ገደብ በመተግበር ረገድ ግን ክፍተት አለ ብሏል።
ዓመቱ በተደጋጋሚ ረዥም ስብሰባዎችን በማድረግ ያሳለፈው ህወሓት በትላንቱ መግለጫውም ወደ ሌላ ስብሰባ ወይም ጉባኤ ለማምራት ዝግጅት ላይ መሆኑ በተያዘው ሐምሌ ወርም 14ኛው መደበኛ ጉባኤው ለማድረግ ውሳኔ ማስተላለፉም አስታውቋል።
ህወሓት “14ተኛ ጉባኤያችን ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ አረጋግጠናል። ስለዚህ የህወሓት ጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በሐምሌ ወር 2016 ዓመተምህረት ውስጥ እንዲካሄድ ወስኖ በቅርቡ ይፋ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን ። በዚህ ግዜ ጉባኤ እንዳይደረግ የሚያደርግ ምክንያት አለመኖሩ ተስማምተናል” ብሏል።
የህወሐት ጽህፈት ቤት
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት፤ የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪያቸውን ከኃላፊነት ማንሳታቸውን ይታወቃል::
ጉዳዩን ልዩ እና ዉስብስብ የሚያደርገው ደግሞ ውሳኔው ያልተጠበቀና ድንገተኛ መሆኑ ነው ተብሏል::
ይህ ደግሞ ብልፅግና ምን እየሆነ እንደሆነ ማሳያ ሊሆን ይችላል ::
29/07/2023
የሰሜን ወሎዋ #አስከ ከተማ ሙሉ በሙሉ በአማራ ፋኖ ላስታ አውራጃ አሳምነው ብርጌድ👍
ፋኖ የአማራ ህዝብ ጋሼና መከታ ነው!
ብቻ እኛ እናሸንፋለን!
"ሰከን!"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Dubai
