Veronica Adane Fan
❤እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ''
ልብ ያለው ይስማ!!
26/05/2024
ጣፋጩ ገዳይ መርዝ!
በሰሜን አንታርቲካ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲፈልጉ የሚዘይዱት ዘዴ አለ፡፡ በበረዶ ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ፤ በላዩ ላይ ጥቂት የበግ ደምን ያደርጉበታል:: ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል፡፡ በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል።
ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል፡፡ በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል፡፡ ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም፡፡ አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው፣ ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል። ከመጠን በላይ ደምም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም።
ይህ ተኩላ ከእኛ ታሪክ ጋር ይቆራኛል፡፡ ብዙዎቻችን ጊዜያችንን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው... ጊዜያችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል... ይጣፍጣልና፤ ጥቂት ብቻ አይበቃንም፤ በፍጥነት እና በኃይልም ህይወታችንን፣ ጊዜያችንን ልሰን እየጨረስነው ነው:: በተቻለህ መጠንም ከስራህ እና ከማሰብ ከሚያስተጓጉሉህ ነገሮች ሁሉ ለማራቅ ሞክር።
©️ድብቁ አእምሮ ድብቁ ኃይል
24/05/2024
23/05/2024
ተሎ በሉ አብረን እንስራበት !!❤
__**⚜ይህ BOT የተሰራው በ እኛ ማለትም በ * 𝔹𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝔽𝕠𝕣𝕖𝕩 * ግሩፓች ሲሆን💡
💸💰💵እናም በዛሬው ቀን በአሁኑ ስዐት ወደ ቦታቸው 1 ሰው ስለጋበዛቹ ብቻ * 10$ * ወይንም (100) ETB ብር በ ወይም በ በፈለጋቹት በታማኝነት እና በፍጥነት እየከፈለ ስለሚገኘው ቦት ሰምተዋልን❔
💲እንግዲያውስ ስለ 📊𝔹𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝔽𝕠𝕣𝕖𝕩 〽️ #ቦት ካልሰሙ
💡𝔹𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝔽𝕠𝕣𝕖𝕩 ች ማለት :- መነሻችን ከኢትዮጵያ የሆነ ከ 10 የማንበዛ ቡድን ስንሆን ራሳችንን 𝔹𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝔽𝕠𝕣𝕖𝕩 ብለን ሰይመን በቴሌግራም ገፅ ጎራ ብለናል🎇
💸እናም በትሬዱ አለም ባካበትነው ረጅም አመት ልምድ ረብጣ ዶላሮችን እኛ * 𝔹𝕣𝕚𝕘𝕙𝕥 𝔽𝕠𝕣𝕖𝕩 * ወደ * Wallet * ችን እያስገባን እንደሆነ በቻናላችንም በግሩፓችንም እያደረግን ሲሆን እናም አዲሱ በሰራነው #ፕላትፎርም እናንተንም ያለምንም ወጪ በማጋራት ብቻ ከምናገኛቸው ረብጣ ዶላሮች ልናካፍላቹ ፈቅደናል🥳
🏅ማለትም 1 ሰው ወደ ኛ ሲጋብዙ 10$ ያሰብን ቢሆንም ሁሉንም ያማከለ እንዲሆን ወደ ET ብር ቀይረንላቹ 1 ሰው ሲጋብዙ 100 ብር ያገኛሉ ማለት ነው🏵
🗯️ከስር⬇️ በተቀመጠው 🌹በ (እርስዎ መጋበዣ ሊንክ) ነክተው አዲስ ሰዎችን ወደ ቦቱ እንዳስባሉ 10$ ማለትም 100 ብር ሰሩ ማለት ነው🥳
💝የ እርስዎ መጋበዣ ሊንክ📌
💸 https://t.me/Meda_Chat_Bot?start=r03211649154
✔️💰⬆️𝔽𝕆ℝ𝕎𝔸ℝ𝔻, ⬆️𝕊ℍ𝔸ℝ𝔼 𝔸𝕃𝕃⬆️ 𝔸ℕ𝔻 𝕎𝕀ℕ 𝕋ℍ𝔼 ℙℝ𝕀ℤ𝔼✔️
#
23/05/2024
22/05/2024
#አትድከም!
፨፨////፨፨
ትልቁ ስህተታችን ስህተት የምንለውን ነገር ስህተት እንደሆነ አምነን ለመቀበል መቸገራችን ነው። ሰዎች ሁሉ አንተ የምታስበውን እንደሚያስቡ፣ ባንተ መንገድ እንደሚያስቡ መጠበቅህ ስህተት እንደሆነ ብታውቅም ከዚህ ሃሳብ መመለስ ግን አላቆምክም። የምታገኘው ሰው ሁሉ አንተ የምታውቀውን የሚያውቅ፣ ባንተ ሃሳብ የሚመራ፣ ካንተ እቅድ ጋር ተመሳሳይ እቅድ ያለው ይመስልሃል። ነገር ግን ሁሉም ሰው የእራሱ የአስተሳሰብ ደረጃ አለው፤ የእራሱ የመረዳት አቅም አለው፤ የእራሱ የእምነት ልኬት አለው። አንተ የመረጥከው ምርጫ ምርጥ የሚሆነው፣ አዋጭ የሚሆነው፣ ትርፋማ የሚሆነው ላንተ ብቻ ነው። ማንም እንዲከተልህ ብትፈልግ ማድረግ የምትችለው ብቸኛ ነገር በምርጫህ ማመንና ሃሳብህን መተግበር ነው። ስህተቶች ስህተት እንደሆኑ ካልታመኑ የመስተካከል እድላቸው እጅግ ጠባብ ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! አትድከም! እኔ ያልኩት ካልሆነ፣ ከእኔ ሃሳብ ውጪ፣ ከእኔ ምርጫ በቀር የሚረባና የሚጠቅም ነገር የለም እያልክ አትድከም፤ እንዲሁ በከንቱ አትልፋ። የሌሎችን ሃሳብ ባትቀበልም የማክበር ግዴታ እንዳለብህ አስታውስ። አስተዋይ እንደሆንክ የተሰማህ ምናልባት ከቀድሞ ማንነትህ ስለተሻሻልክ ወይም የምታያቸውን ሰዎች የበለጥክ ስለመሰለህ ይሆናል። ከሃሳብ የተነሳው መላምትህ በበዛው እራስወዳድነት ሸብቦ ያስቀምጥሃል፤ ሳታስበው ድርጊትህ ሁሉ በሰዎች የሚወደድና ተቀባይነት ያገኘ የሚመስልህን ስሜት እንድታንፀባርክ ያደርግሃል፤ እያደር ካንተ የተሻለ ሰው እንደሌለና ካንተ በቀር ትጉም ያለው ተግባር የሚፈፅም ማንም እንደማይኖር ማመን ትጀምራለህ። እኔ ወይም የእኔ በሚል ሰንሰለት ታስረህ፣ ካንተ በላይ የሰዎችን ልኬትና ደረጃ በእራስህ ሃሳብ ለመገደብ ስትሞክር ትልቁን ስህተት ትፈፅማለት።
አዎ! መልፋት፣ መድከም፣ ከሰው ጋር መጋጨት፣ መበሳጨት አይጠበቅብህም። ማንም ማመን ስለሚፈልገው ማመን ይችላል፤ መቀበል የሚገባውን መቀበል መብቱ ነው፤ ባሰኘው አቅጣጫ መጓዝ ምርጫው ነው። ለሌሎች እንደግዴታና እንደ ትዕዛዝ ከማሸጋገርህ በፊት እውቀትህ በቅድሚያ ላንተ እንደጠቀመህ፣ እንደተገለገልክበት፣ እንዳተረፍክበት እርግጠኛ ሁን። በሃሳብ ብቻ እየተመራህ ሰዎች ምንም ተጨባጭ ነገር ሳይመለከቱ እንዲቀበሉህ አትጠብቅ። እራሱን የተቀበል፣ ለሃሳቡ እውንነት የተፋለመ፣ ለቃሉ የታመነን፣ ለእቅዶቹ እስከ ጥግ የሚጓዝን ሰው ማንም ላያዳምጠውና ላይከተለው አይችልም። በድርቀት ሳይሆን በተግባርህ አሳምን፤ በሃሳብ ሳይሆን በስራህ አስከትል፤ በውጤትህ ቤተሰብ አፍራ።
#ፎሎዉ
21/05/2024
👉 ወቅት ወቅት ነው! ይለዋወጣል! ይመጣል፣ ይሄዳል፡፡
ስለዚህ . . .
#አንደኛ፡- አሁን ያላችሁበት አስቸጋሪ የወቅቱ ሁኔታችሁ እንደመጣ ሁሉ ይሄዳል፡፡ እስከሚሄድ ግን ታገሱ፣ ተረጋጉ፣ የማይዘልቀው አስቸጋሪ ሁኔታችሁ ዘላቂ ጠባሳ እንዳይተውባችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡
#ሁለተኛ፡- አሁን ያላችሁበት ደስ የሚልና ስኬታማ ሁኔታችሁ እንደመጣ ሁሉ ጊዜው ይለወጥና ፈታኝ ሁኔታ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ የከፍታችሁ ጊዜ እስካለ ድረስ ግን አትዘናጉ፣ እቅድ አውጡ፣ ጠንክራችሁ ስሩ፣ ነገ ላይዘልቅ የሚችለው ይህ መልካም ሁኔታችሁን ተጠቅማችሁ ዘላቂ የሆነንና ነገ የሚሸከማችሁን ነገር ገንቡ፡፡
🙏 ፈጣሪ ያግዘን!
#ፎሎዉ
20/05/2024
👇
ህይወትህ ብኩን የሚያደርጉ ነገሮች፦
• ምርጥ ሃሳቦች በአእምሮህ ዉስጥ እየመጡ በተግባር ካላዋልካቸዉ
• እራስህን ከሌሎች ጋር የምታነጻጽር ከሆነ
• የሚጠቅምህ ነገር ላይ ሳይሆን የማይጠቅምህ ላይ ጊዜህን ካቃተልክ
• ሰዎች ስለኔ ምን ያስቡ ይሆን ብለህ መጨነቅ ከጀመርክ
• ትላንት ስላሳለፍከዉ ህይወት ሁሌ የሚቆጭህ ከሆነ
• ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ
• እቅድህ በጣም ከበዛ
• ሰዉን ለመለወጥ ሁሌ የምትሞክር ከሆነ
• ምንም የማይጠቅም ክርክር ዉስጥ እራስህን ካገኘህ
• ለምትሰራዉ ነገር ደንታ ቢስ ከሆንክ ህይወትህን በጣም እያባከንከዉ ነዉና ንቃ!
#ፎሎዉ
19/05/2024
#ተቃርበሃል!
፨፨/////፨፨
ምንም ነገር ብትጀምር መነሻህ ሃሳብህ ነው፤ በሃሳብህ ውስጥ አሰራሩን፣ ሂደቱንና ፍፃሜውን በዓይነ ህሊናህ ተመልክተሃል፤ የምትጓዘው ርቀት፣ የምትከፍለው ዋጋ፣ የሚደርስብህ ፈተና፣ የምትሻገረው መሰናክል ይህን ያክል ግልፅና ጥርት ያለ ባይሆንም መኖሩን ግን በሚገባ ታውቃለህ። ነገር ግን ያሰብከውና የሆነው ባይጣጣም ብዙ አትደነቅ፤ የመነሻህን ሁኔታ፣ አጀማመርህ፣ የመጣሀውን ርቀት፣ ዋጋ የከፈልክባቸውን ጉዳዮች ብቻ በሚገባ ተገንዘብ። ከምታስበው በላይ ለግብህ መቅረብህን፣ ከእቅድህ በተሻለ ወደ መዳረሻህ መጠጋትህን ለማስተዋል ሞክር። የጀመርከው በቀላሉ አይደለም፤ የመጣሀው መንገድም ቀላል አልነበረም፤ እንዲሁ በቀላሉ ለማቆምም እንዳታስብ።
አዎ! ጀግናዬ..! ይሔ ተስፋ የምትቆርጥበት፣ ወደኋላ የምትመለከትበት፣ በትናንት ውድቀትህ ብርታት የምታጣበት፣ የአድናቂዎችህን ቁጥር እየተመለከትክ ወኔ የምታጣበት፣ ውጪ በምታየው ተቃውሞና ስም ማጥፋት ተደናግጠህ የምታቆምበት ጊዜ አይደለም። ከሚባለው በላይ፣ ካቀድከው በተሻለ ወደ ህልምህ እውንነት ተቃርበሃል፤ ግብህን ለመምታት ትንሽ ብቻ ቀርቶሃል። ከመጣሀው ርጅም ርቀት፣ ካሳለፍካቸው አያሌ ውሳኔዎች፣ ከተለየሃቸው ብዙ ሰዎች፣ በዛው ልክ ከተጎናፀፍካቸው አዳዲስ ወዳጆች አንፃር ብዙ ዋጋ ከፍለሃልና በስተመጨረሻ የምታቆምበት ምክንያት አይኖርም።
አዎ! መጀመር ከባድ ላይሆን ይችላል፣ እስከ መጨረሻው መጓዝ፣ የጀመሩትን ከዳር ማድረስ፣ ግብን መምታት ግን ከባዱ ነገር ነው። ምክንያቱም ለመጀመር ሃሳብህ ብቻ በቂ ነው፤ ተነሳሽነትህ፣ ጊዜያዊ ስሜትህ፣ ወኔህ ብቻ በቂ ነው። ከዳር ለማድረስ፣ እስከ መጨረሻው ለመጓዝ፣ ግብን ለመምታት ግን ወጥነት ያስፈልግሃል፤ ተግሳፅ (discipline) ያስፈልግሃል፤ የማይሻር የማይለውጥ፣ የማይናወጥ የማይረበሽ የግል አቋምና መሰረታዊ እምነት ያስፈልጋል፤ ፈተናዎችን እንደ ድልድይ፣ ችግሮችን እንደ እድል፣ ውጣውረዱንም እንደ ብርታት መሳሪያ መመልከት ያስፈልጋል። የማቆም ስሜት ሲሰማህ፣ ተስፋ መቁረጥ ስትጀምር፣ ወኔህ ሲከዳህ፣ ፅናትህ ሲፈተን፣ ትዕግስትህ ሲብረከረክ የመጠህበትን ረጅም መንገድ ተመልከት፣ የቀረህን ተንሽ ርቀት አስተውል። ከምታስበው በላይ ተቃርበሃልና በፍፁም እንዳታቆም በርታ፣ ጉዞህን ቀጥል።
#ፎሎዉ _ሼር _ላይክ
18/05/2024
Big shout out to my newest top fans! Riccardo Spiriticchio, Asseged Demisse, Haylu Desta, Kb Kb, አብዱሠላም አህመድ, Endalk Gm, Hiwan Maarg, Nahom Nahom, Romi Seyoum, Aweke Byen, መቅደስ እያዩ, አበበ ጌጡ
17/05/2024
👉 ለፍተን ያገኘነው ነገር እና በስጦታ ያገኘነው ነገር ልዩነት የሚፈጥርብን ለምንድነው? ስለገንዘብ ነው እማወራው። አብዛኛዎቻችን 2ሚሊዮን ብር ሎተሪ ቢወጣልን የምንጠቀምበት መንገድ የተለየ ነው። ቤት እንገዛለን ወይም እንዝናናበታለን ዱባይ ወይ ፓሪስ ቲኬት ቆርጠን አሪፍ የመዝናኛ ፓርክ ውስጥ እናሳልፋለን። ምን አገባን ገንዘቡ ቢያልቅ ለፍተን አላመጣነው። በአለም ላይ በተደረገ ጥናት ሎተሪ የሚደርሳቸው ሰዎች ስለገንዘቡ ግድ እንደማይሰጣቸው እና የትም ቢጠፋ ምንም እንደማይመስላቸው አረጋግጠዋል። ሎተሪ የደረሳቸውን ሰዎችም ህይወት ሲመረመር ተመልሰው የነበሩበት ላይ ተገኝተዋል።
👉 ነገር ግን በተመሳሳይ 2ሚሊየን ብር ለፍታችሁ ብታገኙት ምን ታደርጋላችሁ? ወይ ባንክ ታስቀምጣላችሁ ወይ የሆነ ስራ ላይ ታፈሱታላችሁ ወይም ደግሞ ትቆጥቡታላችሁ። ሮልፍ ዶብሊ እንደዚህ ሲል ይጠይቃል ፦ ለፍታችሁ ያመጣችሁትም 2 ሚሊዮን ብር በስጦታ የተበረከተላችሁም 2 ሚሊዮን ብር አንድ ነው። ለፍታችሁ ስላመጣችሁት የሚቀየር ብር የለም ይላል።
👉 ይሄ ነገር ብዙዎቻችን ላይ ይሰራል በበአል ቀን በልደት ቀን የምናገኛቸውን ብሮች ቤተሰብ የሚሰጠንንም ብር የትም ለማጥፋት ግድ አይሰጠንም። ይህ የራስን የማግነን አባዜ ኪሳራ ውስጥ ይጥለናል። በነገራችን ላይ እኛ ለፍተን ከምናመጣው ብር በላይ በስጦታ እና በተለያዩ የበአል ዝግጅቶች ላይ የምናገኛቸው ብሮች ብዙ ናቸው። እናም ገንዘብን መቆጠብ እና በትክክለኛ ቦታ ላይ ማዋል አግባብ ነው። ለፍታችሁ አመጣችሁትም ሳትለፉ ብር ብር ነው። ስለሆነም በትክክለኛው እና አግባብ በሆነው ቦታ ላይ አስቀምጡት።
መልካም ቀን❤❤❤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Address
Dubai
Opening Hours
| 10:12 - 15:07 |
