ሰለ corona virus
Stay @ home
28/03/2020
https://www.facebook.com/271276609964528/posts/862394690852714/?app=fbl
የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የተላለፈው መልእክት ላይ የተለያዩ ብዥታዎች ታይቷል ።
ነገር ግን የምርምሩን ሂደት በድጋሜ ለመግለጽ እንወዳለን
የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱ ለማከም የሚያስችል የመድሀኒት ምርምር የመጀመሪያ የቤተ ሙከራ መሰረታዊ የምርምር ሂደትንና ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግን በስኬት አልፏል፡፡
ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን የመጀመሪያ ምርምር ሂደትን አልፎ ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ለማከም እንዲሁም መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ወደ ቀጣይ የምርምር ሂደት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ መግለጫ የተሰጠ በመሆኑ ሙሉ መልእክቱን በትላንትናው እለት ባያያዝነው ቪዲዮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሌሎች ተጨማሪ የምርምሩ ሂደት መረጃዎችንም በቀጣይ የምንገልጽ ይሆናል።
27/03/2020
https://www.facebook.com/123960474361367/posts/2890805044343549/?app=fbl
ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ምርመራ የቫይረሱን ምልክት ማሳየታቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።
ቦሪስ ጆንሰን አሁን ላይ ራሳቸውን ማግለላቸውንም ነው ያስታወቁት።
የመንግስት ስራዎችንም በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደሚመሩም ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
27/03/2020
https://www.facebook.com/123960474361367/posts/2890568084367245/?app=fbl
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 መድረሱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ ኮቪድ19ን በተመለከተ በዛሬ እለት መግለጫ ሰጥቷል
መጋቢት 3/2012 ዓ.ም የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ አራት (4) ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) ደርሷል፡፡ የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-
ታማሚ 1፡ የ72 ዓመት ሞሪሸሳዊ ሲሆኑ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከኮንጎ ብራዛቪል የተመለሱ ናቸው፡፡ መጋቢት 13፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖርት በማደረጉ በተደረገላቸው የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 6 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 2፡ የ61 ዓመት የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ ከታማሚው በተገኘው መረጃ መሠረት ግለሰቡ የውጭ የጉዞ ታሪክ ባይኖራቸውም በስራ ባህሪያቸው ምክንያት ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ግንኙነት ነበራቸዉ፡፡
ግለሰቡ መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም የህመም ስሜት ሲሰማቸው ራሳቻውን አግልለው እንደቆዩና መጋቢት 16፣2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄዱ ሲሆን ተቋሙም ሪፖርት ባደረገው መሰረት በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
በአሁኑ ወቅት ታማሚው በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 24 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን የማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 3፡ የ28 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የመጨረሻ ጉዞዋም መጋቢት 12፣ 2012 ዓ.ም እስራኤል ሀገር ደርሳ የተመለሰች ናት፡፡ ግለሰቧም በቀን 16፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል፡፡
በአሁኑ ወቅትታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡ ከታማሚዋ ጋር ግንኙነት የነበራቸው 7 ሰዎች በክትትል ላይ የሚገኙ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌሎች ሰዎችን ማጣራት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ታማሚ 4፡ የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ስትሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት ቢሆንም የበሽታው ምልክት ከታየባቸው ሰዎች ጋር የነበራት ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ እና ግለሰቧም በቀን 17፣ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙዋ ተረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት ታማሚዋ በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላት ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት እስከ አሁን 718 የላራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 33 በ24 ሰዓት ( መጋቢት 17 ጥዋት 1፡00 ሰዓት እስከ መጋቢት 18 ጥዋት 1፡00 ሰዓት) ውስጥ የተከናወነ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision
27/03/2020
https://www.facebook.com/154163327962392/posts/3014191858626177/?app=fbl
Using to***co products can increase your chance of getting COVID-19
❗️Bringing your 👐 to your 👄 can transfer the virus into your body
❗️Sharing to***co products can transmit the virus between people
❗️Tobacco weakens your respiratory system making you more vulnerable to the virus
21/03/2020
I agree
21/03/2020
https://www.facebook.com/154163327962392/posts/2999579190087444/?app=fbl
Protect yourself from the coronavirus:
-Wash your 👐 frequently
-Maintain social distancing
-Avoid touching 👀,👃and 👄
-Practice respiratory hygiene
-If you have fever, cough and difficulty breathing, seek medical care early
-Stay informed
Thank you Cristiano Ronaldo for spreading WHO advice on COVID-19!
3 new corona virus case in mama Ethiopia.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
12386669

23/04/2020
28/03/2020