Selam wolde

Selam wolde

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Selam wolde, Health/Beauty, Addis Ababa.

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 08/07/2026
21/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ መሆንን ምክንያት በማድረግ ከብልፅግና ፓርቲ የቀረበ የምስጋና መልዕክት፤

እጅግ የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን፣
የተከበራችሁ የፖለቲካ ማኅበረሰብ አባላትና የምርጫው ባለድርሻ አካላት፤

ዛሬ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲን በተግባር ያሳዩበት፣ ታሪካቸውን በደማቁ የጻፉበት እና አፍሪካ ስለ ራሷ በራሷ መወሰን እንደምትችል ለአለም ያበሰሩበት ታላቅ ምዕራፍ መመዝገቡ ይፋ ተደርጓል! በታሪካዊው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ሕዝባችን ትናንትን በማከም እና ነገን በፅኑ መሠረት ላይ በመተለም፣ የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ለማድረግ ፋና ወጊ ለሆነው ለብልፅግና ፓርቲ ዳግም ታላቅ ኃላፊነትና አደራ ሰጥቷል። ብልፅግና ፓርቲ ይህንን ታላቅ ሕዝባዊ አደራ የተቀበለው በስኬቱ ሳይኩራራ፣ ጉድለቶቹን እያረመ ሕዝብን በቅንነት ለማገልገልና ቃልን በተግባር ለማረጋገጥ ባለው ፅኑ እምነት ነው። ለዚህ ታላቅ ክብር መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጠንን የዴሞክራሲ ውል በታላቅ ትሕትና እና በከፍተኛ አክብሮት እንቀበላለን።

ይህ የምስጋና መልዕክት እኛን ለመረጡን ዜጎች ብቻ የቀረበ አይደለም፤ ይልቁንም ያሻቸውን አማራጭ በመምረጥ መብታቸውን የተጠቀሙ፣ በካርዳቸው ድምፅ በመንፈግም ቢሆን ሂደቱ ሕጋዊና ሰላማዊ እንዲሆን የበኩላቸውን የተወጡ ዜጎችን ሁሉ ያጠቃልላል። ምክንያቱም የእያንዳንዱ ዜጋ ተሳትፎ የሀገራችን ዴሞክራሲ እውነተኛ አሸናፊ እንዲሆን አድርጓል።

በዚህ ምርጫ ሂደት ውስጥ በግልጽ መለየት ያለበት መሠረታዊ እውነት አለ፡- የብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ አግኝቶ መንግሥት የመመሥረት መብት ማግኘቱ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይ ሰንቆ ውጤታማ ጉዞ እያደረገ እንዳለ ፓርቲ እንደ ትልቅ እድል የሚወሰድ ሲሆን፤ የምርጫው ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሓዊና ተዓማኒ ሆኖ መጠናቀቅ ግን የውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ እና የመላው ሕዝቧ ስትራቴጂያዊ አሸናፊነት ማረጋገጫ ነው!

ይህ ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሙ የተለመደ የፖለቲካ ውድድር ወይም ወቅታዊ ኩነት አልነበረም። ይህ ምርጫ የውስጥና የውጭ የሴራ መረቦችን የበጣጠሰ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በተግባር ያደመቀ፣ የዴሞክራሲ ተቋሞቻችንን ብስለት ያጎለበተ ታላቅ የታሪክ እመርታ ነው። ኢትዮጵያ በማንኛውም ውጫዊ ጫና ሳትበገር፣ ሙሉ በሙሉ በራሷ ሁለንተናዊ አቅም ያከናወነችው ይህ ታሪካዊ ክንውን ሀገር በቀል ዴሞክራሲን እና አህጉራዊ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ በመሆኑ ለመላው አፍሪካ ኩራትና ተምሳሌት ሆኗል።

ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መሳተፋቸው የሕዝባችንን የፖለቲካ ንቃት የሚያሳይ ሲሆን፣ የሕዝብን ድምፅና ሉዓላዊ ፈቃድ ማክበር የመንግሥትና የማንኛውም የፖለቲካ ተዋናይ ቀዳሚ ተግባር መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። በምርጫው የኢትዮጵያ ጠላቶች ሀገርን ለማወክ የሸረቡት ተንኮልና መፍጨርጨር በሕዝባችን ብስለት ሙሉ በሙሉ እንዲመክን ተደርጓል።

የዚህ ታሪካዊ ስኬትና የኢትዮጵያ አሸናፊነት መረጋገጥ ያለ ባለድርሻ አካላት ተጋድሎ ሊታሰብ አይችልም። በመሆኑም ፓርቲያችን ብልፅግና ለምርጫው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናውንና አክብሮቱን ያቀርባል፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ሕዝብ የአገር ህልውናንና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ያለውን የማይናወጥ ወገንተኝነት በተግባር ባሳየበት በዚህ ታሪካዊ የምርጫ ሂደት፣ በተለይም በምርጫው ዕለት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ እግር ጥሎት ሳይሆን ራዕይ መርቶት፣ ብርድና ድካምን በሀገራዊ ፍቅር እያሸነፈ፣ እስከ ሚቀጥለው ቀን ሌሊት 10 ሰዓት ድረስ ለሙሉ 24 ሰዓታት ያለመሰልቸት በታላቅ ትዕግሥትና ዲሲፕሊን ተሰልፎ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱን ለመጠቀም ያሳየው ታሪካዊ ቁርጠኝነትና የፖለቲካ ብስለት ለፓርቲያችን ብልፅግና ብቻ ሳይሆን ለመላው ታዳጊ ዴሞክራሲዎችና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የተግባር ማስተማሪያና የሉዓላዊነት ተምሳሌት በመሆኑ፣ ለዚህ አስተዋይና ስልጡን ሕዝብ ፓርቲያችን ከፍ ያለ አክብሮቱን፣ ኩራቱንና ጥልቅ የሆነ ሕዝባዊ ምስጋናውን በታላቅ ትሕትና ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱን ፍፁም በሆነ ገለልተኝነት፣ በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት፣ በትዕግስትና በሕጋዊነት መርህ በመምራት የኢትዮጵያን ተቋማዊ ነጻነት በዓለም ፊት ስላስመሰከረ የላቀ አድናቆትና ምስጋና ይገባዋል።

42 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከ10 ሺህ በላይ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሂደቱ መሳተፋቸው ሕዝባችን አማራጮችን በሰፊው መዝኖ እንዲመርጥ አድርጓል። በመሆኑም ከውጭና ከውስጥ ይነፍስ የነበረውን የሀሰት ወጀብ ተቋቁማችሁ፣ ለሰላማዊ የሃሳብ ውድድር እና ለሕግ የበላይነት ያሳያችሁት ስልጡን ቁርጠኝነት ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ባህል ማበብ ታላቅ መሠረት ጥሏል። እናንተ የሕዝብ ሉዓላዊነት አክባሪዎችና የሀሳብ ፖለቲካ ታጋዮች ናችሁና ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባችኃል።

የፌዴራልና የክልል የጸጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ሕዝቡ ያለምንም ስጋት በነጻነት ወጥቶ ድምፁን መስጠት እንዲችል ሌት ተቀን በመሥራት፣ መስዋዕትነት በመክፈል እና ሀገርን ከጥፋት ኃይሎች በጽናት በመጠበቅ ታላቅ ኃላፊነት ተወጥተዋል። እናንተ የሀገር ጠበቃ እና የሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ናችሁና ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባችኃል።

የሚዲያ ተቋማት ሕዝቡ በመብቱ እንዲጠቀም፣ ነፃና ሚዛናዊ የምርጫ ድባብ እንዲፈጠር ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ሙያችሁን አክብራችሁና ለሀገራችሁ በፅኑ ታምናችሁ ላበረከታችሁት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባችኋል።

የሀገር ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ በመንቀሳቀስ፣ ለዜጎች ሰፊ የዴሞክራሲና የመራጮች ትምህርት በመስጠት፣ የሕዝባችን የፖለቲካ ንቃት እንዲያድግና መብቱን እንዲረዳ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና ተጫውታችኋል። በምርጫው ዕለትም በሺዎች የሚቆጠሩ ታዛቢዎችን በየምርጫ ጣቢያው በማሰማራት ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ሀገር በቀል አቅማችሁንና ተቋማዊ ነጻነታችሁን በተግባር ስላሳያችሁ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ይገባችኋል።

የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ “ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለውን ታላቅ መርህ በተግባር በማሳየት፣ አህጉራዊና ቀጠናዊ ተቋማቶቻችን ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እንደሚችሉ ዳግም አስመስክረዋል። የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የአህጉራችን ኩራትና የተምሳሌትነት ማሳያ መሆኑን በመመስከር፣ የምርጫውን እውነተኛነትና ተዓማኒነት በዓለም መድረክ ከፍ ስላደረጋችሁ፤ ላሳያችሁት ፅኑ ፓን-አፍሪካዊ ወንድማማችነት፣ ቀጠናዊ አጋርነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ፓርቲያችን ብልፅግና የላቀ ምስጋናውንና አክብሮቱን ያቀርባል።

ሌሎች ቀጣናዊ ተቋማትና ወዳጅ ሀገራትም የኢትዮጵያን ተጨባጭ እውነታ በትክክል በመረዳት፣ አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በልዩ ትኩረት ለተከታተላችሁ እና ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁን በመመስከር አዎንታዊና ጠቃሚ ግብረ መልሶችን ለሰጣችሁ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባላት፣ ቀጣናዊ ተቋማትና ወዳጅ ሀገራት በሙሉ ፓርቲያችን ብልፅግና የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል። የእናንተ ሚዛናዊና እውነተኛ ምስክርነት የሀገራችንን ተቋማዊ ተዓማኒነት የሚያጎለብት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ጀመረችውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ የሚደግፍ ታሪካዊና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማረጋገጫ በመሆኑ በታላቅ አክብሮት እንቀበለዋለን።

ብልፅግና ፓርቲ በሕዝብ የተሰጠውን አዲስ የዴሞክራሲና ማኀበራዊ ውል መሠረት በማድረግ፣ የሥልጣን ባለቤትነቱ የሕዝብ መሆኑን በተግባር ያረጋግጣል። በቀጣይ ዓመታት መንግሥታችን የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮና አስፍቶ የሚሄድ ሲሆን፣ በተለይም የሕዝብ ጥያቄዎች የሆኑና የጋራ ጥረት በሚጠይቁ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ከሕዝባችንና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሙሉ በመተባበር ምላሽ እንዲያገኙ ርብርብ የምናደርግ ይሆናል።

ከዚህ አንፃር ዘላቂ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈንና የሕግ የበላይነትን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት፣ የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን በስፋት ለመፍጠርና የዜጎቻችንን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ሀገራዊ አስተዋጽኦ ለማሳደግ፣ የተጀመረውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በስፋት በማስፋፋት፣ የቢሮክራሲ ማነቆዎችን በመበጣጠስና የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በቆራጥነት ለመከላከልና የተገልጋዩን ሕዝብ እርካታ በከፍተኛ ደረጃ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት የምንሰራ ይሆናል።

በተጨማሪም በመገባደድ ላይ የሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ በሚገባ በመደገፍ፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን ይበልጥ ነፃ፣ ገለልተኛና ጠንካራ እንዲሆኑ በማጠናከር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ብሔራዊ ጥቅማችንን ማዕከል ባደረገ መልኩ በትብብር በመስራት ገንቢ ሃሳቦቻቸውንና አቅማቸውን ለማካተት የጀመርናቸውን ጥረቶች የምናልቅ ይሆናል።

በአጠቃላይ ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር፣ ምርጫ የሥልጣን መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ መሆኑን በተጨባጭ ያረጋግጣል። ለዚህም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዟችንን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት አጠናክረን ለመቀጠል ለተከበረው ሕዝባችን ዳግም ቃላችንን እናድሳለን!

ብልፅግና ፓርቲ
ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

21/06/2026

በአዲስ አበባ ከተማ የክልል ምክር ቤት ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ አብላጫዉን መቀመጫ አገኘ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማሳወቂያ መርሐ-ግብር አካሄዷል፡፡

ቦርዱ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የምርጫ ክልል በተካሄደዉ የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት አብላጫ መቀመጫ ያገኙትን ተወዳዳሪዎች ይፋ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 የምርጫ ክልሎች ለክልል ምክር ቤት ከቀረቡ 158 መቀመጫዎች መካከል ብልጽግና ፓርቲ 134 መቀመጫዎችን ሲያገኝ ኢዜማ 8 መቀመጫዎችን ማግኘቱን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ ይፋ ባደረገዉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት መሰረት ፡-

👉 የአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ብዛት - 10

👉 አጠቃላይ የክልል ምክር ቤቱ መቀመጫ ብዛት - 158

👉 ብልጽግና ፓርቲ - 134 መቀመጫዎች

👉 ኢዜማ ፓርቲ - 8 መቀመጫዎች

👉 አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 4 መቀመጫዎች

👉 ህዳሴ ፓርቲ - 2 መቀመጫዎች

👉የኦሮሞ ነጻነት ግንባር - 2 መቀመጫዎች

👉 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - 2 መቀመጫዎች

👉 ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት - 2 መቀመጫዎች

👉 የወላይታ ህዝቦች የነፃነት ንቅናቄ - 1 መቀመጫ

👉 የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ - 1 መቀመጫ

👉 የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - 1 መቀመጫ

👉 አቶ ዳንኤል ጌታቸዉ ጋረደዉ የግል ተወዳዳሪ - 1 መቀመጫ ማግኘታቸዉን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ 7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ 1 ሚሊዮን 957 ሺህ 676 መራጮች ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 96 መቶ የሚሆኑት መራጮች በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
AMN-Addis Media Network

21/06/2026

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን የሰጡት ድምፅ የህዝብ አደራና የክብር ማህተም ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን የሰጡት ድምፅ ከዜጎች የተሰጠ ታላቅ አደራ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይነት ማረጋገጫ የክብር ማህተም መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

በዚህም ቦርዱ እንዳሳወቀው፤ ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ከተሰጠባቸው እና ውጤታቸው ይፋ ከሆኑ የምርጫ ክልሎች አብላጫ ድምጽ አግኝቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከእያንዳንዱ ህዝብ ድምፅ የተሰጠ ታላቅ አደራ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይነት ማረጋገጫ የክብር ማህተም ነው ብለዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን የሰጧቸው ድምጾችም የዕድገትና የብልፅግና ማህተም መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በድምፁ አመኔታ የሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከባዱን ኃላፊነት በጸጋ በመቀበል ለህዝብ የልማት፣ የዕድገትና ብልጽግና ትሩፋት በርትተው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

21/06/2026

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ስኬታማ ተሳትፎ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ እርምጃ ነው - የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያውያን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያደረጉት ስኬታማ ተሳትፎ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ልዑክ እና የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት የማሳወቂያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ ኢትዮጵያውያን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሳዩት ተሳትፎ ለስኬታማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ እርምጃ መጀመራቸውን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ላለው ለዚህ ስኬታማ ጉዞ የአፍሪካ ህብረት ትልቅ አድናቆት እንዳለው አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ህብረት፣ አባል ሀገራቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር በሚያደርጉት ጉዞ ፍጹም ገለልተኛ፣ ሚዛናዊ እና ነጻ በሆነ መንገድ የመደገፍ ግዴታ እንዳለው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዑሁሩ ኬንያታ የሚመራ የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ አሰማርቶ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስትም የአፍሪካ ህብረት ልዑክ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርትን በማስመልከት መግለጫ ማውጣቱን አስረድተዋል።

ህብረቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለነበረው ግንኙነት አድናቆታቸውን ገልጸው፤ በዚህች ታላቅ ሀገር ቀጣይነት ላለው መሻሻልና ለዴሞክራሲ መጎልበት በጋራ ለመሥራት ቃል እንገባለን ብለዋል።

አህጉራችን ዴሞክራሲን ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ የላትም በማለት፣ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራትና ባለድርሻ አካላት ሰላማዊ፣ አካታችና ሙሉ ተሳትፎ የሰፈነበት ዴሞክራሲን ለማስፈን ቁርጠኛ ሆነው እንዲቀጥሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa