Teslo
Making closest interaction with my group members and relatives.
20/07/2025
🗿እዩ ጩፋ ካውንስሉን ይቅርታ ጠየቀ❕❔
➖➖➖➖➖➖➖➖
የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በቅርቡ በሚዲያ ላይ እንደሰማችሁት ለተፈጠሩት ክፍተቶች ከካውንስሉ የስነ መለኮት ኮሚሽን እና የህግ ኮሚሽን ጋር ዉይይት ካደረገን በኋላ ቤተክርስቲያናችን በጉዳዩ ላይ ስንፀልይና ስንመካከር ቆይተን የደረስንበትን ስምምነት እንደሚከተለው እናቀርባለን።
ካውንስሉን እና የካውንስል አመራሮች በተመለከተ በቴሌቭዥን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ለተጠቀምናቸው ያልተገባ ቃላት ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን።
ከዚህ ቀን ጀምሮ ካውንስሉን ከሚመሩ መሪዎቻችን ጋር በቅርበት እየተነጋገርን እንደ አባት እና ልጅ ተቀራርበን የክርስቶስን ወንጌል መንፈሳዊ ጨዋነት ተከትለን ቀዳሚዎቻችንን አክብረን ለማገልገል የተስማማን መሆኑን እየገለፅን ካውንስሉም ይቅርታችንን ተቀብሎ አባታዊ በሆነ መንገድ እየመከረን እና እያስተማረን እንዲመራን በመተማመን ይህንን መግለጫ እንደ ቤተክርስቲያን አውጥተናል።
💄Via ~ FastMereja❕🥰
02/05/2025
ኢትዮጵያዊው/የወላይታ ተወላጅ/ ዛሬ ቼልሲን ይገጥማል..| ISAK ALEMAYEHU | ኢትዮጵያዊው/የወላይታ ተወላጅ/ ዛሬ ቼልሲን ይገጥማል..| ISAK ALEMAYEHU | Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channe...
02/05/2025
02/05/2025
02/05/2025
03/04/2025
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኋላ ላለፉት 7 ዓመታት እስከ አለም አቀፍ ደረጃ ያከናወኗቸው ቁልፍ ተግባራት ምንድናቸው ?
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ፣ በ2018 ዓ.ም. በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ከማስረከባቸው ጊዜ ጀምሮ፣ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሰላም፣ የልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ እና የፖሊሲ ማዘጋጀት መስኮች ላይ ያለእረፍት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ቀጥለዋል።
በተለይም፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በሚይዟቸው አመራር ቦታዎች፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው ሚናቸው እንዲሁም ለሰላም እና ለልማት የሚደረጉ ጥረቶች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አፍሪካዊ ሀገራት ላይ ያላቸው ተጽዕኖ በማያሻማ ሁኔታ ይታወቃል። ይህ የዛሬው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ልዩ ጥንቅር እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2025 ዓ.ም. ድረስ ያለውን የእሳቸውን ዋና ዋና ተግባራት መካከል ከብዙ በጥቂቱ ያቀርባል።
በዚሁ ልዩ ጥንቅር ላይ የአቶ ኃይለማርያም ከ2018 በኋላ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ሚና በተመለከተ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ፣ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት የሚደረጉትን ጥረቶች፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት የሚሰሩ ስራዎች፣ በአፍሪካዊነት እና በአለም አቀፍ ድምፅ ላይ ያደረጉትን ትኩረት እንዲሁም ለፀና አፍሪካ የሚሰሩ ፅንሰ-ሀሳቦች ላይ ያላቸውን አቋም በተመለከተ ዝርዝር ይዘናል።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እ.ኤ.አ 2018 ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኃላ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እንዲሁም በአለምአቀፍ ደረጃ የተሳተፉበትና እየተሳተፉ ያሉበት ዝርዝር መረጃዎች በጥቂቱ እነሆ 👇
👉 ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ቦርድ አባል። እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምረው፥
👉 የአፍሪካ ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የትረስት ቦርድን አባል ሆነው ተመረጡ። እ.ኤ.አ ከ2021 ጀምረው፥
👉 የአፍሪካን ዋይልድላይፍ ፋውንዴሽን የግሎባል ትረስት ቦርድ አባል። እ.ኤ.አ ከ2022 ጀምረው፥
👉 በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥበቃን በማሳደግ እና #የአፍሪካ ድምጽን በመወከል መሳተፍ እ.ኤ.አ ከ2021፥
👉አሊያንስ ፎር ኤ ግሪን ሪቮሉሽን አፍሪካ (ኤጂአርኤ) የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ሊቀ መንበር
👉 የትሬድማርክ አፍሪካ ቦርድ ሰብሳቢ እ.ኤ.አ ከ2025 ጀምረው፥
👉 የታንዛንያ ፕሬዝደንታዊ ከፍተኛ ምክር ቤት አባል በመሆን በሀገሪቱ ፕረዚዳንት ተሹመው እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምረው፥
👉 በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገው የመጀመሪያው ተቋም ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በማቋቋም ወደ ተግባር ማስገባት፥
👉 በጃፓንና በአፍሪካ ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ላበረከቱት አስተዋፅኦ እስፕሪንግ ኢምፔሪያል የተባለውን ጃፓን ለውጪ ዜጎች የምትሰጠው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2019፥
👉 በአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ በዓለ ስመታቸው የአፍሪካ ልዑካንን በመምራት እንዲገኙ ተጋብዘው በብቸኝነት ተካፍለዋል። እ.ኤ.አ በ2025፥
👉 የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክ ንግድ ቡድን (The A-eTrade Group) የበላይ ጠባቂ ሆነው መሾም። እ.ኤ.አ ከ2021 ጀምረው፥
👉 የወቅቱ የትሬድማርክ አፍሪካ የቦርድ ሰብሳቢ በተጨማሪ ከእ.ኤ.አ 2019 ጀምሮ የግዙፉ በአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ጥምረት (AGRA) የቦርድ ሊቀመንበር፥
👉 መቀመጫውን ብራሰልስ ቤልጂዬም ያደረገ አንድ ታዋቂ በሰላምና የሰላማዊ ስልጣን ሽግግር ላይ የሚሰራው ድርጅት ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ በራስ ፍቃድ ሥልጣን ያሸጋገረ የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ መሪ" በማለት ዕውቅና መስጠት። እ.ኤ.አ በ2019፥
👉 እ.ኤ.አ 2018 ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኃላ ከባለቤታቸው ከቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ዘይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር በመሰረቱት ትልቅ ፋውንዴሽን አማካይነት የተለያዩ አለምአቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ተጨባጭ ስራ እየሰሩ ናቸው።
አጠቃላይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምረው 2025 ድረስ ያከናወኑት ቁልፍ ተግባራት👇
👉 የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ለውጥ ተነሳሽነት (ACCI) መሪነት አማካይነት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተከሰቱትን ችግሮች ለመቋቋም፣ ለምሳሌ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የምግብ ዋስትና እጦት፣ የሚያስችሉ የፖሊሲ ማዕቀፎችን እንዲያዘጋጁና እንዲተገብሩ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል።
👉 የተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋሮችን በማስተባበር የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የአቅም ግንባታ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት አድርገዋል።
👉 በአፍሪካ ቀጠና በተለይም በአጎራባች ሀገራት የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ላይ ተሳትፈዋል።
👉 በተለያዩ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የአፍሪካ ቀጠና ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የጋራ ርብርብ አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተዋል።
👉 በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በመሳተፍ ስለ ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ድምፃቸውን አሰምተዋል። በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ፣ በልማት እና በሰላም ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን አቋም በግልጽ አሳይተዋል።
👉 በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ገንቢ አስተዋጽኦ በማበርከት በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ በመሳተፍ የፖለቲካ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ብዙዎች የመሳሰሉትን ከፍተኛ ኃላፊነት በማስረከብ አስገንዝበዋል።
👉 ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ ካስረከቡ በኃላ ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካይነት በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት በሚረዱ ጉዳዮች ላይ እውቀታቸውን አካፍለዋል።
👉 በተለይም የአፍርካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ ማግኘት አለበት፣ የአፍሪካውያን ዕድገት ዕድል በእውቀት ላይ በተመሠረተ በአፍሪካውያን አንድነትና መተባበር ውስጥ ይገኛል የሚለውን የፀና አቋማቸው በተለያዩ መድረኮች አንፀባርቀዋል።
👉 በሚገርም ሁኔታ በሰላማዊ መንጠድ ስልጣናቸውን ከለቀቁ 2 ዓመት በኃላ "እኛ ኢትዮጵያዊን ከጦርነት አስተሳሰብ መውጣት አለብን፣ ግዜያችንን በአግባቡ ተጠቅመን ትኩረታችንን በልማትና ዕድገታችን ላይ እናድርግ" በሚል ዕለት በታሪካዊው ህዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት በጀመረበት ቦታ በአካል በመገኘት ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።
👉 በየጊዜው ዋጋው እየጨመረ የሚገኘው እውነተኛ ማንነት ባለቤት፣ በርካታ መሪዎች በስልጣን ሙጭጭ ብለው ለማድረግ ያልደፈሩትን በተግባር ያሳየ፣ ተግባሩንም በመኖር እያሳየ የሚገኝ፣ የወጣበት ማህበረሰብ እሴትን እንዲሁም ፈጣሪንም ስልጣን ላይ ተጨማልቀውና ከህዝብ ሰርቀው ያላስነቀፉ የህያው ታሪክ ባለቤት የሆኑት።
👉 በአፍሪካ ቀጠና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፣ በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በመሳተፍ በአፍሪካ ቀጠና የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው።
👉 የአፍሪካ ቀጠና ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ: በተለያዩ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የአፍሪካ ቀጠና ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ የጋራ ርብርብ አስፈላጊነትን እያሳሰቡ ነው።
👉 የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ ማግኘት አለባቸው የሚል ፅኑ አቋም፥ በተለያዩ መድረኮች ላይ በመሳተፍ የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን መፍትሔ ማግኘት እንዳለባቸው እና የአፍሪካውያን ዕድገት ዕድል በአፍሪካውያን አንድነትና መተባበር ውስጥ እንደሚገኝ አፅንኦት ሰጥተዋል።
👉 በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት፥ በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ በመሳተፍ የፖለቲካ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን እያሳሰቡ ነው።
👉 ከፖለቲካ ተሳትፈው በተጨማሪ ትውልድ በመልካም ስብዕና እንዲገነባ እንዲሁም እውነተኛ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲከተል የወንጌል አገልግሎት እንዲሰጡ ከኢትዮጵያ ከሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ህጋዊ የቅስና ማዕረግ ተሰጥትዋቸው የተለያዩ አለማት በመዞር እያገለገሉ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከለቀቁ በኋላ ላለፉት ሰባት ዓመታት በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ያከናወኗቸው ተግባራት በእጅጉ የሚደነቁ ናቸው። በሰላማዊ መንገድ ስልጣን በመልቀቅ ለአፍሪካ አርአያ በመሆን፣ በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በመሳተፍ የአፍሪካን ድምፅ በማስተጋባት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት የጎላ አስተዋፅኦ በማድረግ የህያው ታሪክ ባለቤት በመሆን ቀጥተኛ አዎንታዊ ተጽእኖ ያላቸው መሆኑን በርካቶች የሚመሰክሩት ሀቅ እንደሆነ ይታወቃል።
በተጨማሪም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት በኋላ፣ በአፍሪካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የአስተዳደር፣ የሰላም፣ እና የልማት መሪ ሆነው እንዲቀጥሉ የቻሉት፣ በሰላማዊ ሽግግር ወቅት ያሳዩት ምሳሌያዊ አመራር እና ለህብረተሰቡ ያላቸው ቁርጠኝነት ሲሆን፣ ይህም በተለያዩ የአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ያላቸው እንቅስቃሴ በግልጽ ይታያል።
ከዚህ ባሻገርም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያሳዩት ጥረት፣ እንዲሁም በልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ፣ የኢትዮጵያን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረታዊ እርምጃ ነው። አቶ ኃይለማርያም በሰላማዊነት፣ በአገራዊ አንድነት፣ እና በአፍሪካዊ ወኪልነት ላይ ያተኮረው ርብርብ፣ ለወደፊት ትውልድ የሚተርፍ ታሪካዊና በምሳሌያዊነት የዘለቀ እንደሆነ በርካቶች ይመሰክራሉ።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜
👁👀 ሚዲያ👏
29/03/2025
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Website
Address
Iasi
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 17:00 |
| Sunday | 09:00 - 17:00 |
