Etcare
An official page of Etcare, Etcare is a company that produces and sell beauty care products
17/07/2026
3ኛ ሳምንት ከነቢል ሰመሩ ጋር
ያሳለፍናቸው 2 ሳምንታትን የነበሩ ድንቅ መድረኮች በላቀ የስልጠና አቅም ሊደገም ነው
ቅዳሜ ረፋድን በኢቲኬር ካሳለፍናቸው ሳምንታት የቀጠለ ቀጥተኛ ሽያጭን በተግባር ከኖረ ስኬትን በህይወት ልምዱ ካደረገ የረጅም ዘመን አሰልጣኝ ስራ ፈጣሪ እና የቀጥተኛ ሽያጭ ባለሙያ አንደበት አይተኬ የሆነ የስልጠና ጊዜን እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።
አሰልጣኛችንን
ነቢል ሰመሩ
ስራ ፈጣሪ የሪል ስቴት አልሚ አምራች እና የሚዲያ ሆስት
የረጅም አመት አለም አቀፍ የቀጥተኛ ሽያጭ ኢንዱስትሪ ልምድ ከተኖረ ስኬት ጋር ያካበተ አሰልጣኝ እና የቀጥተኛ ሽያጭ ባለሙያ
ቅዳሜ በልዩ ሁኔታ ለኢቲኬሪያን የምርት አስተዋዋቂዎች ብቻ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ።
በኢቲኬር ስራ የጀመራችሁ በምርት አስተዋዋቂነት ቆይታ ያላችሁ የኢንዱስትሪውን ፍልስፍና እና አሰራር በዚህ አሰልጣኝ ለመካፈል ተጋብዛችኋል።
ነገ ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡00
በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ
መግቢያው ተከፍሏል
Etcare
እሁድ ደርሷል!
ያለፈውን ድምቀት በትልቁ ልንደግመው ሀዋሳን በኢቲኬሪያንስ ልናሸበርቃት ቀኑ ደርሷል።
እሁድ ሀምሌ 12 እንገናኝ
16/07/2026
የህይወት ክህሎት ስልጠና በኢቲኬር አየርጤና ቅርንጫፍ።
ሳምንታዊው የኢቲኬር የህይወት ክህሎት ስልጠና ዛሬ ከኢቲኬር ማስተር አሰልጣኝ ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉ ጋር ተከናውኗል።
መለወጥን የሻቱ ኢቲኬሪያንስ በንቃት የተሳተፉበትን ይህንን መድረክ የኢቲኬር ፕሮፌሽናል አሰልጣኙ አቤል ንጉስ መርቶታል።
ሪጅናል ዳይሬክተሮቻችን ለሀዋሳ ዝግጁ ናቸው
እሁድ ሀምሌ 12 ቀኑ ነው
16/07/2026
ሪጅናል ዳይሬክተሮቹ የደመቁበት መድረክ
ትናንት በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት በነበረው የመሪነት ስልጠና 3ቱ የኢቲኬር ሪጅናል ዳይሬክተሮች ደማቅ የሆነ የስልጠና መድረክን አከናውነዋል።
ከኢቲኬር ደሴ ቅርንጫፍ ሪጅናን ዳይሬክተር አረቡ ሁሴን እና ያሬድ አሰፋ፣ከኢቲኬር ባህርዳር ቅርንጫፍ ሪጅናል ዳይሬክተር መለሰ አያሌው በመድረኩ ከልምድ እና ተሞክሯቸው የተቀዱ የመሪነት ሀሳቦችን በድንቅ ብቃት አካፍለዋል።
Etcare
16/07/2026
https://youtu.be/KE7sgAmsT1Y?si=DH83o3dGa7uz2zCR
ስኬትን እንደ ማግኔት ሆነን እንሳበው! 2ኛ ሳምንት ስልጠና ከነቢል ሰመሩ ጋርየቀጥተኛ ሽያጭ አለም አቀፍ ባለሙያው ነቢል ሰመሩ ከኢቲኬሪያንስ ...
እየደረሰ ነው!
3 ቀናት ብቻ
13/07/2026
https://youtu.be/y_ph0aGtaFk?si=2w8hwYTW2jgXjDDY
ማይረሳ ጊዜ በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት ! የሁለት ቀናት ስልጠና ማጠቃለያ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞችና ክልሎች የተውጣጡ የኢቲኬር አባላት ለ2 ተከታታይ ቀናት ሲከታተሉት የነበረውን...
13/07/2026
ደማቁ ቀን እሁድ
እሁድ በኢቲኬር ከታላቅ መሪዎች እና አሰልጣኞች ጋር የመሪነት ስልጠናችንን መገባደድ ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ ተደርጓል።
በርካታ መሪዎች እና አሰልጣኞችን ተጋባዥ እንግዶች በነበሩበት በዚህ ዝግጅት ላይ የድርጅታችንን መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ እና የማኔጅመንት አካላት በጋራ ተገኝተውበታል።
ከስራ አረፍ ተብሎ ከማህበራዊ ሀላፊነት በኋላ በጋራ በማእድ እና በመዝናኛ የታጀበው መሰናዶ ደማቅ ትውስታን ጥሎ አልፏል።
13/07/2026
ኢቲኬር እና ማህበራዊ ሀላፊነት
ኢቲኬሪያንስ የትናንት እሁድን እንዴት አሳለፉ?
ኢቲኬር ከተለያዩ የክልል ቅርንጫፎች የተውጣጡ መሪዎችን ለ2 ቀናት የቆየ የ መሪነት ስልጠናን ሲያገባድድ የእንኳን ደስ አላችሁ የመዝጊያ የምሳ መሰናዶ አከናውኗል።
ታዲያ ይህ የኢቲኬሪያንስ የምሳ መሰናዶ ጅማሮውን ያደረገው ኢቲኬር ከሚከተላቸው መርህዎቹ አንዱ የሆነውንለሌሎች ማሰብ ግድ ማለትን ተግባራዊ በማድረግ ነበር።
በኢቲኬር ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ ለሚገኙ ወገኖቻችን በታላላቅ መሪዎቻችን አማካኝነት የማእድ ማጋራት በማድረግ ባሉበት አካባቢ በመዘዋወር በመጎብኘት እና የፍቅር ማእድን በማጋራት አሳልፈዋል።
በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ መሪዎችም የድርጅቱን መርህ ከቃል ወደ ተግባር በማዋል በእንቅስቃሴው ላይ በንቃት ተሳትፎ አድርገዋል።
Etcare
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Https://maps. App. Goo. Gl/9awY8x3TpHfJixMi 9
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 07:00 |
| Tuesday | 08:00 - 13:00 |
| Wednesday | 08:00 - 13:00 |
| Friday | 08:00 - 13:00 |
| Sunday | 08:00 - 13:00 |
