Brand Fitness Machines
ዘመናዊ ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት ማሽኖችን ከኛ ያገኛሉ። 0953012345 ላይ ይደውሉልን።
14/06/2026
የስኳር ህሙማን ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 3 ቅድመ ጥንቃቄዎች
1. የህክምና ባለሙያ ማማከር
• ማንኛውም ዓይነት የአመጋገብ ለውጥ ከማድረጋችሁ በፊት ወይም ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት የህክምና ባለሙያ ብታማክሩ ተመራጭ ነው።
2. የደም ስኳራችሁን መከታተል
• ከስፖርት በፊት እና በኋላ የደም ስኳራችሁን ቼክ ማድረግ ይኖርባችኋል። ይህም ስፖርት በደም ስኳራችሁ ላይ ያለውን ተጽዕኖ ለመረዳት ይጠቅማችኋል። ኢንሱሊን የምትወስዱ ከሆነ ደግሞ የደም ስኳራችሁን በደንብ መከታተል አለባችሁ። የደም ስኳራችሁ ከመቶ በታች ከወረደ ቀለል ያለ ነገር ብትበሉ ይመረጣል። ከዛ ከ30 ደቂቃ በኋላ በመለካት የደም ስኳራችሁ ጥሩ ከሆነ ስፖርት መስራት ትችላላችሁ። ስፖርት ስትሰሩ አጠገባችሁ ከረሜላ ወይም ሌላ አነስ ያለ ጣፋጭ ነገር መያዝ ይኖርባችኋል። ይህ ድንገተኛ የሆነ በጣም ዝቅተኛ የደም ስኳር ወይም Hypoglycemia ከተፈጠረ ቶሎ ለማስተካከል ይረዳችኋል። በተለይ ኢንሱሊን የሚጠቀሙ ህሙማን ላይ ይህ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው።
3. ለስፖርት የሚሆን ጫማ ማድረግ
• ከስኳር ህመም መዘዞች አንዱ የእግር ቁስለት ነው። ይህ መዘዝ እግራችሁን የማትንከባከቡት ፣ ጽዳቱን የማትጠብቁት እና ጥፍራችሁን የማትቆረጡ ከሆነ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው። እንዲሁም ለስፖርት የማይሆን ደረቅ ጫማ አድርጋችሁ መስራት የለባችሁም። ስለዚህ እግራችሁን በየቀኑ ማየት እና መንከባከብ ፣ ጥፍራችሁን በየጊዜው መቆረጥ እና ለስፖርት የሚሆን ጫማ አድርጋችሁ ብትሰሩ ይመረጣል።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
13/06/2026
የስኳር ህሙማን ስፖርት ስትሰሩ የምታገኟቸው ሦስት ጥቅሞች
ስፖርት የደም ስኳርን ይቀንሳል። እንዲሁም ሰውነታችን ለኢንሱሊን ሆርሞን የሚሰጠውን ምላሽ ይጨምራል።
የተለያዩ ጥናቶችን እንደሚያሳዩት
1. በሳምንት ቢያንስ በጠቅላላ ለሁለት ሰዓት መራመድ በራሱ በስኳር በሽታ ምክንያት የሚመጣ የልብ በሽታን ለመቀነስ ይረዳል። የበለጠ በተራመዳችሁ ቁጥር ደግሞ የበለጠ ጥቅም ታገኛላችሁ።
2. ስፖርት ጡንቻ እንድትገነቡ ይረዳችኋል። የጡንቻችሁ መጠን ሲጨምር ጡንቻዎች በከፍተኛ መጠን የደም ስኳርን ይጠቀማሉ። ይህም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል።
3. ስፖርት ከደም ስኳር ልኬት አይነቶች አንዱ የሆነውን HbA1c ን በከፍተኛ መጠን ይቀንሰዋል። ይህ ልኬት ቀን በቀን ከምንለካው የደም ስኳር ልኬት የሚለይ ሲሆን ያለፉትን ሦስት ወራት የደም ስኳር የነበረበት ሁኔታ ያሳያል። ይህም ህመሙ ያለበትን ደረጃ ያሳውቀናል። ኤሮቢክስ ፣ ብረት ወይም ሁለቱን ያካተቱ ስፖርቶች ይህንን ልኬት እንደሚቀንሱ ታይቷል።
እናንተ የምትሰሩት ስፖርት ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
#ስኳርበሽታ
12/06/2026
የመገጣጠሚያ ህመም የሚያስቸግራችሁ ከሆነ መስራት የሌለባችሁ 4 ስፖርቶች
1. ሩጫ
2. ገመድ ዝላይ
3. ከባድ ኤሮቢክስ
4. ቴኒስ
እነዚህ ስፖርቶች በመገጣጠሚያ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳርፋሉ። እንደ ቴኒስ ያሉ ስፖርቶች ደግሞ በድንገት እንድትቆሙ እና አቅጣጫ እንድትቀይሩ በማድረግ ከባድ ተጽእኖ ይፈጥራሉ። እንዲሁም ለረጅም ሰዓት መቆምም ህመም ያስከትላል። የመገጣጠሚያ ህመም የሚያስቸግራችሁ ከሆነ ውሃ ዋና ፣ ሳይክል መንዳት ወይም ረጋ ያለ እርምጃ ማድረግ ትችላላችሁ።
እናንተ ህመሙን ለመቀነስ የምታደርጉትን ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
11/06/2026
ስፖርት ስትሰሩ ራስ ምታት የሚያስቸግራችሁ ለምን ይመስላችኋል?
1. ውሃ የማትጠጡ ከሆነ
• በላብ መልክ የሚወጣውን ውሃ የማትተኩት ከሆነ ለራስ ምታት ያጋልጣችኋል። ከዛ በተጨማሪ ከባድ ድካም ይሰማችኋል። ስለዚህ ስፖርት ስትሰሩ ውሃ ብትጠጡ ተመራጭ ነው።
2. ዝቅተኛ የደም ስኳር
• በቂ ምግብ ሳትበሉ ስፖርት የምትሰሩ ከሆነ በደማችሁ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ዝቅ እንዲል በማድረግ ራስ ምታት ያስከትላል። ስለዚህ ከስፖርት በፊት ሃይል ሰጪ የሆኑ እንደ አጃ ወይም ሙዝ ያሉ ምግቦችን ብትመገቡ ጥሩ ነው።
3. ከልከ በላይ መስራት
• ከልክ በላይ ስትሰሩ በአንጎላችሁ ውስጥ ውጥረት በመጨመር የራስ ምታት ያስከትላል።
ነገር ግን ራስ ምታቱ ለቀናት ከቀጠለ ወይም ከተለያዩ ከባድ ምልክቶች ጋር የሚታይ ከሆነ ወደ ህክምና ብትሄዱ ይመከራል።
ስፖርት ስትሰሩ የሚያስቸግራችሁ ህመም ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
10/06/2026
ጭንቀት ክብደት እንድትቀንሱ ሚያደርጋችሁ እንዴት ይመስላችኋል?
1. የምግብ አምሮትን በመቀነስ
• ጭንቀት በአንዳንድ ሰዎች ላይ የምግብ ፍላጎታቸውን ሲጨምረው በሌሎች ላይ ደግሞ ፍላጎታቸውን ይቀንሰዋል። ይህም በጊዜ ሂደት ትንሽ እንዲመገቡ ያደርጋቸዋል።
2. ካሎሪን በማቃጠል
• ስንጨነቅ ከሚለቀቁት ሆርሞኖች ውስጥ አንዱ ሰውነታችን በፍጥነት ካሎሪ እንዲያቃጥል ያደርገዋል።
ጭንቀት በውፍረት ላይ ያለው ተጽእኖ የተወሳሰበ ነው። በአንዳንድ ሰዎች ላይ ውፍረት ሲያመጣ ሌሎችን ደግሞ እንዲከሱ ያደርጋቸዋል። ይህንን መረዳት ጭንቀትን በመቆጣጠር በሰውነታችን ክብደት ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለማስቀረት ይረዳናል።
እናንተ ሲጨንቃችሁ ትወፍራላችሁ ወይስ ትከሳላችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
09/06/2026
ከወለዳችሁ በኋላ ስፖርት መጀመር ያለባችሁ መቼ ይመስላችኋል?
እርግዝናው ጤናማ ከነበረ እና የወለዳችሁት መደበኛ በሆነ መልኩ ከሆነ ከስድስት ሳምንት በኋላ ስፖርት መጀመር ትችላላችሁ። እንዲሁም ስሜታችሁን እያያችሁ መጀመር እንደምችሉ እስኪሰማችሁ ድረስ መቆየትም ትችላላችሁ።
ነገር ግን የወለዳችሁት በኦኘሬሽን ከነበረ ወይም ወሊዱ ላይ ያጋጠሙ የተለያዩ አይነት ችግሮች ከነበሩ ግን ስፖርት ከመጀመራችሁ በፊት ከሚከታተላችሁ የህክምና ስፔሻሊስት ጋር መመካከር ይኖርባችኋል።
እናንተ በእርግዝና ወቅት ምን ያህል ኪሎ ጨመራችሁ? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
08/06/2026
ክብደት መግፋት ቁመትን የሚያሳጥረው እንዴት ይመስላችኋል?
ወጣቶች እና ታዳጊዎች ክብደት በሚገፉበት ወቅት ቁመት ያሳጥራል የሚል አስተሳሰብ አለ። ይህ ግን የተሳሳተ አመለካከት ነው። ይህንን የሚደግፍ ሳይንሳዊ መረጃ የለም። ክብደት በመግፋት የሚመጡ ጉዳቶች የሚከሰቱት በትክክለኛ አቋም እና ቴክኒክ የማንገፋ ከሆነ ነው። ይህ ደግሞ በማንኛውም እድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል። በተለይ ከባድ ብረቶችን ስትገፉ ለአደጋ የመጋለጥ እድላችሁ ሰፊ ነው። ስለዚህ ከባድ ብረት የምታነሱ ከሆነ ከአሰሪ ጋር በመሆን ብትገፉ ይመከራል።
እናንተ የምታውቁት በስፖርት ዙሪያ ያለ የተሳሳተ አመለካከት ምንድነው? ኮሜንት ያደርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
07/06/2026
የምግብ ፍላጎታችሁ እየወረደ አስቸግሯችኋል? እነዚህን 3 ነገሮች ስታደርጉ የምግብ ፍላጎታችሁ የተስተካከለ ይሆናል።
1. ስፖርት
ስፖርት መስራት የምግብ ፍላጎታችሁን በከፍተኛ መጠን ይጨምረዋል ።
2. ከምግብ በፊት ውሃ አለመጠጣት
ከምግብ በፊት ውሃ ስትጠጡ ሆዳችሁን በመሙላት መመገብ የምትችሉት የምግብ መጠን ይቀንሰዋል።
3. የምትወዱትን ምግብ መመገብ
ሽታቸው ደስ የሚሉ እና የምትወዷቸውን ምግቦች ስትበሉ የምግብ ፍላጎታችሁ ይጨምራል።
ነገር ግን የምግብ ፍላጎታችሁ ለሳምንታት ከወረደ ፣ ሳትፈልጉ ክብደት ከቀነሳችሁ ፣ ምግብ ለመዋጥ የሚያስቸግራችሁ ከሆነ ፣ማስመለስ እና ማቅለሽለሽ ካጋጠማችሁ ወደ ህክምና በመሄድ ምርመራ ብታደርጉ ይመከራል።
እናንተ የምግብ አምሮታችሁን ለመጨመር የምታደርጉት ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
06/06/2026
ክብደት መጨመርን አስቸጋሪ የሚያደርጉ 4 ነገሮች
1. ዝቅተኛ የምግብ አምሮት
ጭንቀት ፣ የሆርሞን መዛባት ወይም የተለያዩ ምክንያቶች የምግብ አምሮትን ሊቀንሱ ይችላሉ።
2. ጀኔቲክስ
ከቤተሰብ የወረሳችሁት ቀጠን ያለ ሰውነት ከሆነ በአንጻራዊነት ክብደት ለመጨመር ይከብዳችኋል። ይህ ማለት የተሻለ ጄኔቲክስ ካላቸው ሰዎች አንጻር የበለጠ መስራት ይኖርባችኋል።
3. ፈጣን ሜታቦሊዝም
ሰውነታችሁ ካሎሪን በፍጥነት የሚያቃጥል ከሆነ ክብደት ለመጨመር ብዙ ካሎሪ ከማያቃጥሉት አንጻር ተጨማሪ መመገብ አለባችሁ።
4. የተለያዩ ህመሞች
እነዚህ የምትመገቡት ምግብ በሚፈልገው መጠን እንዳይመጠጥ ያደርጋሉ። ከዛ በተጨማሪ የምግብ አምሮታችሁን ይቀንሳሉ።
እናንተ ክብደት እንዳትጨምሩ ያደረጋችሁ ምክንያት ምን ይመስላችኋል? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
05/06/2026
ስፖርት በተደጋጋሚ የምታቋርጡ ከሆነ ማድረግ ያለባችሁ ሶስት ነገሮች
1. ቀስ ብላችሁ መጀመር
ወዲያውኑ ከባድ ብረት ለመግፋት ወይም ከባድ ስፖርት ለመስራት አትሞክሩ። ከዛ ይልቅ ቀስ በቀስ የስፖርቱን ክብደት እና ርዝመት እየጨመራችሁ መሄድ ይኖርባችኋል ።
2. የእረፍት ቀን መመደብ
በሳምንት የተወሰነ የእረፍት ቀን መመደብ አለባችሁ። ይህም ከልክ በላይ አንዳይደክማችሁ እና ስፖርት እንዳይሰለቻችሁ ያደርጋል።
3. ዲስፕሊን መገንባት
ስፖርት የመስራት ሙዳችሁ ቢመጣም ባይመጣም ራሳችሁን አስገድዳችሁ መስራት ይኖርባችኋል። ስፖርት ደስ ሲላቸው ብቻ የምትሰሩ ከሆነ በጊዜ ሂደት ማቋረጣችሁ አይቀርም። ለዚህ የሚሆነው መፍትሄ ደግሞ ዲስፕሊን መገንባት ነው።
እናንተ ስፖርት ሳታቋርጡ ለመስራት የምታደርጉት ምንድነው? ኮሜንት ያድርጉልን።
ይህንን መረጃ ያዘጋጀላችሁ ብራንድ ፊትነስ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ የስፖርት መሳሪያዎችን የሚያስመጣ እና የሚሸጥ ድርጅት ነዉ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፎሎ ማድረግ እንዳትረሱ፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
