Arada Giorgis Specialized Medical Center
Welcome to Arada Medical Center, your trusted healthcare provider. We specialize in Internal Medicine and Dermatology, offering expert care to our community.
Our dedicated team of professionals is committed to delivering compassionate
የጆሮ ታምቡር መበሳት ችግር
ልጆች ለወላጆቻቹህ ውድ ስጦታ አበርክቱ
በኢትዮጵያ ውስጥ ገዳይ የሆኑ 7 በሽታዎች
ከግብረ ስራ ግንኙበት በኋላ ሽንታችሁን የማትሸኑ ከሆነ ....
ሽሮ ከበላቹህ በኋላ እነዚህ ነገሮች ይሰማቹሃል
ሽንት ቤት ውስጥ ስልክ ይዘው ሰዓታት ያሳልፋሉ?
ብዙዎቻችን እንደ ቀልድ የምናያቸው ነገር ግን ለከባድ የኪንታሮት (Hemorrhoids) ህመም የሚያጋልጡ 4 መጥፎ ልማዶች!
1️⃣ መጸዳጃ ላይ በስልክ ቲክቶክ እና ፌስቡክ እያዩ መቆየት፦ በታችኛው የሰውነታችን የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ግፊት ይፈጥራል።
2️⃣ የሆድ ድርቀትን ቸል ማለት፦ በቂ ውሃና አትክልት አለመመገብ ስንጸዳዳ በኃይል እንድንአምጥ በማድረግ የደም ስሮችን ያቆስላል።
3️⃣ መጸዳዳት ሲመጣ አምቆ መያዝ።
4️⃣ በስራ ምክንያት ሳይንቀሳቀሱ ለረጅም ሰዓት ወንበር ላይ መቀመጥ።
ጤናዎን አደጋ ላይ የሚጥሉ እነዚህን ልማዶች ዛሬውኑ ያቁሙ!
📞 ለበለጠ መረጃ +251989070707
ሽንት ቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓት የመቀመጥ 3 አስከፊ ጉዳቶች!⚠️
ብዙዎቻችን ሽንት ቤት ውስጥ ስልክ በመጠቀም ወይም በሌላ ምክንያት ለረጅም ሰዓት የመቀመጥ ልማድ አለብን። ነገር ግን ይህ ልማድ በጤናችን ላይ የሚያስከትላቸውን 3 አደገኛ ጉዳቶች ያውቃሉ?
1️⃣ የሆድ ድርቀት እና የሰገራ ወደ ኋላ መመለስ፦ ሽንት ቤት ውስጥ ለረጅም ሰዓታት መቆየት የሰውነታችንን የተፈጥሮ የሰገራ ማስወገድ ሂደት ያዛባል። ይህም ሰገራ ተመልሶ ወደ አንጀት እንዲገባ በማድረግ ለከፋ የሆድ ድርቀት ይዳርጋል።
2️⃣ የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoids)፦ ሰገራ ሳይመጣ ለረጅም ሰዓት ተቀምጦ ማማጥ በፊንጢጣ አካባቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል። ይህ ጫና የደም ስሮቹ እንዲለጠጡና እንዲያብጡ በማድረግ ለኪንታሮት በሽታ ያጋልጣል።
3️⃣ የአንጀት መውጣት (Re**al Prolapse)፦ ለረጅም ሰዓት ተቀምጦ ማማጥ አንጀትን ተሸክመው የሚይዙ ቲሹዎችንና ጅማቶችን ያረግባል። በዚህም ምክንያት የትልቁ አንጀት የመጨረሻ ክፍል (ሬክተም) ከቦታው ተንሸራቶ ወደ ውጪ ሊወጣ ይችላል።
💡 ጤናዎን ለመጠበቅ እና መሰል ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት Follow ማድረግ እንዳይረሱ!
ጆሮዎ ውስጥ የሚጮኸው ድምጽ የጆሮ ሳይሆን... የደም ግፊት ምልክት ሊሆን እንደሚችል አስበው ያውቃሉ?
በድንገት ጆሮዎ ከተደፈነ ወይም የልብ ትርታን የሚመስል ድምጽ ማስተጋባት ካጋጠመዎት፣ ይህ ደም በከፍተኛ ግፊት ሲፈስ ጆሯችን አጠገብ ባሉ ደም ስሮች ላይ የሚፈጥረው ጫና ነው። የደም ዝውውር መስተጓጎል ድንገተኛ የመስማት አቅም መቀነስን (የጆሮ ስትሮክ) ሊያመጣ ይችላል።
ይህንን ቪዲዮ አይተው ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ፤ ጤና አይገዛም!
ወንድ ልጅ ግንኙነት ቀን በቀን ቢያደርግ ምን አይነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል?
ይህ ብዙዎች የማይናገሩት ግን ለወንዶች ጤና ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው! በየቀኑ የዘር ፈሳሽ መልቀቅ እነዚህን 2 ትልልቅ ችግሮች ያስከትላል፦
1️⃣ የዘር ፍሬ ጥራት (S***m Quality) መቀነስ፦ ሰውነት በቂ ጥራትና ብዛት ያለው የዘር ፍሬ ለማምረት ጊዜ ያጣል።
2️⃣ የሆርሞን መዛባት፦ የቴስቶስትሮን (የወንድነት ሆርሞን) መጠን እንዲቀንስ እና የኢስትሮጂን መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።
የወንድነት እና የብልት ጤና ምርመራዎችን በዘመናዊ ማሽኖች እና በስፔሻሊስት ሀኪሞች ዘንድ ለማግኘት ያማክሩን።
📞 +251989070707
እንጀራ በየቀኑ የሚበላ ሰው ሰውነት ውስጥ ምን ይፈጠራል?
ብዙ ጊዜ እንጀራን እንደ ቀላል ምግባችን እናየዋለን፤ ግን በየቀኑ ስንመገበው በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠረው ለውጥ ያስደንቃል። በተለይ የጤፍ እንጀራ ከሆነ ጥቅሙ እጥፍ ነው!
ወደ ዋናው ነጥብ ስንመጣ፡
1️⃣ የብረት (Iron) ማዕድን ማከማቻ፡ ጤፍ ከስንዴ እና ከሩዝ በላቀ ሁኔታ የአይረን ይዘት አለው፤ ለደም ማነስ ችግር ተጋላጭ ለሆናችሁ፣ በተለይም ለሴቶች እና ለህጻናት ከዚህ የተሻለ የተፈጥሮ መድኃኒት የለም።
2️⃣ የሆድ እና የአንጀት ጤንነት፡ እንጀራ ለምግብ መፈጨት ስርአታችን በጣም የዋህ ነው፤ ሆድን አያከብድም፤ የምግብ መፈጨት ስርአትን በማስተካከል ሰውነት ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጠምጥ ያደርጋል።
3️⃣ የሃይል ምንጭ፡ በውስጡ ያለው ጥራት ያለው ካርቦሃይድሬት ለዕለታዊ እንቅስቃሴያችን የሚያስፈልገንን ጉልበት በወጉ ይሰጠናል።
ጤናችንን ለመጠበቅ መጀመሪያ የምንመገበውን ማወቅ አለብን። ይህ መረጃ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ያካፍሉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Ethiopia Addis Ababa Piassa
Addis Ababa
