Meznagnia Media

Meznagnia Media

Share

Celebrating 10 Years.

Salem Media (ሳሌም) is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.

31/05/2026

ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ ያለዉ ካናዳዊው አሊ አህመድ ለፊፋ የዓለም ዋንጫ ለካናዳ ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ተመረጠ።

ለእንግሊዙ ኖሪዊ ናች ሲቲ ክለብ በአማካኝ ስፍራ የሚጫወተው የ 25 ዓመቱ ወጣት አሊ አሕመድ፣ በአሜሪካ ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ሀገሮች አስተናጋጅነት ከJune 11 - July 19,2026 ዓ.ም ለሚካሔደው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን 26 ተጫዋቾች ዝርዝር ዉስጥ ተካተተ።

ቀጭኑ እና ጠይሙ አሊ፣ ከልጅነቱ ጀምሮ ከእኩዮቹ ጋር ኳስ ሲጫወት ግሩም ችሎታ ስለነበረው አሰልጣኞቹ ፔሌ እያሉ ነበር የሚጠሩት። አሊ ለአራት ዓመታት ለቫንኩቨር ዋይት ካፕስ ቡድን የተጫወተ ሲሆን፣ የካናዳ የአመቱ ተስፋ ያለው ምርጥ ወጣት ተጫዋች ተብሎ ተሸለሞ ነበር። የእንግሊዙ ኖርዊች ሲቲ ክለብ በዚህ አመት ከገዛው በኋላ ፊርማውን አኑሮ በክለቡ በመጫወት ላይ ይገኛል።

በካናዳ ሀገር፣ በቶሮንቶ ከተማ ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ተወልዶ ያደገው አሊ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ በካናዳ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ጐልቶ የሚታይ ኮከብ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

“በአለም ዋንጫ ላይ የመጫወት ህልሜ እውን ሆኗል::” በማለት አሊ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ በቡድኑ ውስጥ በመካተቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል ።

አሊ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ኢትዮጵያውያንን የሚወክል ፣ ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የተገኘ፣ ብቸኛው እና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ ያለው በዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፍ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ በታሪክ ዉስጥ ይመዘገባል።

መዝናኛ ሚዲያ፣ ዳንኤል ገብረማርያም

23/05/2026

የአንጀሊና ጆሊ ሴት ልጅ ፣ ዘሀራ ማርሊ ጆሊ በሳይኮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከስፔልማን ኮሌጅ አገኘች።

ጤና አዳም ተብላ በትውልድ መጠሪያ ስሟ ትታወቅ የነበረቸው የዛሬዋ ዘሀራ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ 2005 ዓ/ም ገና የ6 ወር ህፃን እያለች ነበር በአንጀሊና ጆሊና በብራድ ፒት ወላጅ አሳዳጊነት በማደጎ ልታድግ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተወሰደቸው።

ዛሬ ላይ ዘሀራ የ 21 አመት ወጣት ሆና በሳይኮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከስፔልማን ኮሌጅ አግኝታ ባሳለፍነው ቅዳሜ ተመርቃለች።

ዘሃራ እውቁን በአትላንታ ከተማ የሚገኘውን ስፔልማን የጥቁሮች ኮሌጅ የተቀላቀላቸው ከ4 ዓመት በፊት ነበር። በደመቀ ስነ-ስርዓት በተከበረው የምርቃት ስነ ስርዓቷ ላይ አምስቱን ወንድም እና እህቶቿን ጨምሮ እናቷ አንጀሊና ጆሊ ስትገኝ ፣ ብራድ ፒት ግን በቦታው አልተገኘም።

ከአንጀሊና ጆሊ ጋር የጠበቀ ቅርበት እንዳላት የሚነገርላት ዘሀራ፣ ግንኙነታቸውና ፍቅራቸው እጅግ ጥልቅ እንደሆነ ይነገራል። “ዘሀራን ያገኘሁበት ቀን እጅግ የተባረከ ቀን ነበር ::” የምትለው ጆሊ ፣ ዘሀራን ስትገልፃት “እጅግ ሰው አክባሪ፣ ባለ ብሩህ አዕምሮ እና አስተዋይ ልጅ ናት::”ብላ ትገልፃታለች።

ዘንድሮ 569 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስመረቀው ስፔልማን ኮሌጅ ከተመሰረተ 144 ዓመትን ያስቆጠረ ሲሆን ፣ ከዘንድሮ ተመራቂዎቹ መካከል የታዋቂው አሜሪካዊ ዘፋኝ ሉዳ ክሪስ ሴት ልጅ ካርማ ብሪጂስ ትገኝበታለች። ከተመራቂዎቹ መካከል 7ቱ ሙሉ አራት ነጥብ በማግኘት በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።

ዘሀራ በምረቃ ስነ ስርዓቷ ላይ ቀድሞ ትጠራበት ከነበረዉ ዘሀራ ፒት ጆሊ ከሚለው መጠሪያ ስሟ ፣የማደጎ አባቷ የብራድ ፒት መጠሪያ ስም የሆነው ፒት የሚለው የማሀል ስም ማርሊ በሚል ተተክቶ ዘሀራ ማርሊ ጆሊ ተብላ እንድትጠራ ወስናለች።

ይህ አዲስ የስም ስያሜ የጋዜጠኞችን ትኩረት አግኝቶ ስለ ዘሀራ አዲስ መጠሪያ ስም አንጀሊና ጆሊ በጋዜጠኞች ተጠይቃለች፣ የቦብ ማርሊ አድናቂ እንደሆነች የሚነገርላት አንጀሊና ጆሊ ስትመልስም፣ “ልጇ ስሟ እንዲቀየር የራሷ የዘሀራ ዉሳኔ መሆኑን ገልፃ ፣ አዲሱ የመሃል መጠሪያ ስሟን ስያሜ ምርጫ ማማከሯን እና ቦብ ማርሊን ለመዘከር በማሰብ የስሟ የመሀል መጠሪያ ማርሊ እንዲሆን አድርገናል፡:” ብላለች።

ጋዜጠኛው “በሄድሽበት ቦታ ሁሉ ዘሀራ አለች ለምንድን ነው ? “ ብሎ ሲጠይቃት ፣ “ዘህራ በጣም የምወዳት ልጄ ናት፣ አሁን ደግሞ ጓደኛዬ ሁናለች ፣ ሁሌ አጠገቤ ስትሆን ሙሉ የሆንኩ ይመስለኛል ::” ብላ መልሳለታለች ፣ ጆሊ ቀጥላም ዘሀራ የፊልም ተዋናይ የመሆን ፍላጐት እንደሌላት ገልፆለታለች።

ፍቅር ጥግ የለውም ፣ ፍቅር ከልብ የሚመነጭ ምንጭ ነው፣ አንጀሊና ጆሊ ጐዳና ላይ ተጥላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተገኘቸው ዘህራ ንፁህ የእናትነት ፍቅር ሳትቆጥብ ሰጥታታለች ፣ ፈጣሪ አብዝቶ ይባርክሽ አንጀሊና ጆሊ::

https://youtu.be/kdUsAPFMyYg?si=GdCKeBJPWHUfme0N

መዝናኛ ሚዲያ፣ ዳንኤል ገብረማርያም፣

09/05/2026

የብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) የግል የሕይወት ፍልስፍና እና ቆይታ

| ታዋቂው የጥበብ ሰው ብርሃኑ ተዘራ (ላፎንቴን) ሕይወትን በቀላል መንገድ የመምራት ልምዱንና የግል አመለካከቱን የሚገልጽበትን የመጀመሪያ ክፍል ቃለ መጠይቅ አቅርቧል።

በዚህ ዝግጅት ላይ አርቲስቱ ነገሮችን ሳያወሳስቡ በመኖር ውስጥ ስላለው ሰላም እና ስለ ቆይታው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሙሉውን ውይይት በሊንኩ በመከተል መመልከት ይቻላል።
https://youtu.be/s9n-tOraPZk?si=-WDWN9Zfb6wgJD54


#ጌጡ #ጌጡተመስገን

04/05/2026

የሻኪራ የብራዚልየሙዚቃ ኮንሰርት ብዙ ተመልካችን በማግኘት ሪከርድስበረ።

ኮሎምቢያዊቷ ታዋቂ ድምጻዊት ሻኪራ ‘ኤል ዶራዶ ዎርልድ ቱር’ የተባለውን እና በዓለም ላይ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች እየተዘዋወረች የምታቀርበውን ማራቶን የሙዚቃ ኮንሰርት ባሳለፍነው ቅዳሜ በብራዚሏ ሪዬ ዲጄኔሮ ከተማ አካሒዳ 2 ሚሊዮን ህዝብ አደባባይ በመውጣት የሙዚቃ ዝግጅቱ ታዳሚ ሆኗል።

በዚህም መሰረት በሪዮ ዲ ጄኔሮ ከተማ አጠገብ በሚገኘው ኮፖካታና ቢች የተካሔደው እና መግቢያው በነፃ በነበረው የሻኪራ ኮንሰርት በርከት ያለ ተመልካች በቀጥታ የተከታተለው በመሆን የዓለምን ክብረ ወሰን ሰብሯል።

የአራት የግራሚ አዋርድ ሽልማት አሸናፊዋ ሻኪራ ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ በስፖኒሽ ሙዚቃ ላይ የነገሰች እና 12 አልበሞችን የለቀቀች ሲሆን ከ95 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች በአለም ላይ ተሽጦላታል።

የ49 ዓመቷ ሻኪራ ከቀድሞው የባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የ39 ዓመቱ ጄራርድ ፒኬ ጋር ከ10 ዓመታት በላይ አንድ ላይ በትዳር ቆይተው፣ ሁለት ልጆችን አፍርተው ፣ትዳራቸው በፍች መጠናቀቁ ይታወቃል።

መዝናኛ ሚዲያ / መዝናኛ@meznagnia

01/05/2026

የሰው ባል አዲስ የኢትዮጵያ ፊልም በዩቲዩብ ለተመልካች ቀረበ

| በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሰው ባል የተሰኘው አዲስ ፊልም በታዲያስ ፊልም የዩቲዩብ ገጽ ላይ በይፋ መለቀቁ ተበሰረ።

በድ ራማና በፍቅር ታሪክ ላይ ያተኮረው ይህ ፊልም በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ጥራት ያላቸው ስራዎችን በዲጂታል አማራጮች ለተመልካች ለማድረስ የሚደረገው ጥረት አካል ነው።

የሰዎችን ማህበራዊ ህይወትና የፍቅር ግንኙነት በጥበብ የሚዳስሰው ይህ ስራ አሁን ላይ በዩቲዩብ የሚገኝ ሲሆን ተመልካቾች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲመለከቱት ተጋብዘዋል።

ጥበብን በቅርበት የሚያቀርበውን ይህን ፊልም ከስር በተቀመጠው ሊንክ ማግኘት ይቻላል።

ፊልሙን ለመመልከት ይህን ይጫኑ፦ https://youtu.be/kdUsAPFMyYg?si=rmyfcd_USoSfzDNL

#አዲስፊልም #የሰውባል #ጥበብ #ኢትዮጵያ #የፍቅርፊልም #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


50 S Pickett Street
Addis Ababa
22304

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00