Gym life style
Maintain our body weight gain,weight loss&weight balance
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Berhane Gebreslassie, Gonsamo Gobena
13/10/2024
English learn ŵ me on TikTok 37 Followers, 532 Following, 0 Likes - Watch awesome short videos created by English learn ŵ me
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mekbib Adela Arsenal, Amir Boyka Jemal, Ãñá Hùmñãsà Kíñg, Siraj Mehamed, Ama Hayelom, Damee Darajee, Miki Miki, Panda Panda
07/01/2023
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!
17/10/2022
??
🎈 አንድ ሳምንት ሰባት ቀን ነው ያለውና ሰባቱም ቀን መስራት ከፈለግክ/ሽ መስራት ትችላላችሁ ግን ደግሞ አንደዛ ስትሰሩ ምን ምን መስራት እንዳለባችሁ ማወቅ ይኖርባችኋል። ጡንቻ ለመገንባት ነው ወይስ ጡንቻን እየገነባችሁ ውፍረት ለመቀነስ ነው ወይም ደግሞ ውፍረት ለመቀነስ ብቻ ነው የምትሰሩት። ግባችሁ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ለመከወን ከሆነ ምን አይነት ኤክሰርሳይሶችን የምትሰሩት የሚለው ጥያቄ ወሳኝነት አለው።
🎈አንድ ጡንቻ/muscle ለመገንባት እስከ 48ሰአታት ይፈጃል። ጡንቻችንን ይበልጥ ባሰራነው ቁጥር የምናርፍበት ጊዜም በዛው ልክ እየጨመረ ይመጣል። ለዚህም ነው በሳምንት ውስጥ የምንሰራቸውን ኤክሰርሳይሶች መከፋፈል ያለብን።
💡እንዴት እንስራ ላላችሁኝ??
1️⃣እየከፋፈላችሁ መስራት፦ይህም ማለት push,pull,leg የሚባለውን ዘዴ መከተል ነው ማለትም መግፋት መጎተት እና እግር ሲሆን
🔑 #ለመግፋት የምንጠቀምበትን የሰውነት ክፍላችንን ማሰራት ደረት ትከሻ እና የኋላ እጅ/triceps.
🔑 ለመጎተት የሚንጠቀምበት የፊት እጅ/biceps እና ጀርባ።
🔑 በመጨረሻም የእግር ይሆናል ማለት ነው።
2️⃣FULL BODY መስራት፦ይህም ማለት ሙሉ የሰውነታችንን ክፍል በአንድ ቀን ማሰራት ነው።
👆 #እነዚህን አንዴት ነው ምንሰራው???
💡 ከላይ አንደገለፅኩት በሳምንት ውስጥ ከሁለት አንድ መርጣችሁ መስራት ትችላላችሁ ወይ (push,pull,leg) ወይም ደግሞ (FULL BODY)
💡 PUSH PULL LEG እነዚህ ስትሰሩ በመጀመሪያው ቀን ለምሳሌ እንበልና PUSH ሰኞ ከሰራችሁ ማክሰኞ ደግሞ PULL እሮብ leg ሰርታችሁ ሰትጨርሱ ሀሙስ ላይ ስትደርሱ ደግሞ ከሰኞ-እሮብ የሰራችሁትን መድገም ይሆናል ማለት ነው።
💡 FULL BODY ምትሰሩ ከሆናችሁ ደግሞ አንድ አንድ ቀን እየዘለላችሁ መስራት ትችላላችሁ።
📌ምን ያህል ቀን እረፍት ባረግ ይሻላል??
💡PUSH PULL LEG በሳምንት ስድስት ቀን ስለምትሰሩት እረፍታችሁ አንድ ቀን ይሆናል።
💡FULL BODY ምትሰሩ ከሆነ ደግሞ ከ3-4ቀን ብትሰሩት በቂ ነው።ዋናው ማወቅ ያለባችሁ FULL BODY ከሰራችሁ በኋላ ከ1-2 ቀን በቂ እረፍት ማድረጋችሁን ነው።
10/10/2022
ህይወት ሪሞት የላትም ተነስ እና ጀምር !
02/10/2022
ስኬት ሂደት ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ በርካታ ውጣውረዶች ይኖራሉ። ከእነዚህም አንዱ የሰዎች አስተያየት ነው። ሰዎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በተለይም እነርሱ ሞክረው ያልተሳካላቸው ከሆነ ወይም ማሳካት ፈልገው ነገር ግን በፍርሃት ሳያደርጉት ቀርተው፣ ወይም አውቀው ሌላው እንዲያሳካው ስለማይፈልጉና በሌሎችም ምክንያቶች ለስኬት እየሮጡ ያሉ ሰዎችን በአትችልም፣ አይሆንም፣ አይሳካም አስተያዬት ወደ ኋላ ሲጎትቱ ብሎም ከሕልማቸው ሲያጨናግፉ ይታያል።
ሆኖም ግን ይህ እንደሚያጋጥመው ያወቀ ማንኛውም የስኬት ተጓዥ ለመጥፎ ሀሳቦችና አስተያየቶች ራሱን ካላስገዛ የፈለገውን የስኬት ጫፍ መርገጥ ይችላል። ማንም በዚህ መንገድ ላይ ያለና ያለፈ ያውቀዋል።
02/10/2022
ሕይወትን እንደ ንሥር አሞራ ኑር!
====================
ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው ፍጡር ነው። ሌሎች ቁራዎችና ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሆነው ከበው ሲጮሁበት ወደ ፀሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል። ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ፀሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋባቸዋል!!
- ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል፣
- ንስር ከ 2.30-3 ሜ ይረዝማል፣
- ንስር ከ5-7 ኪሎሜትር ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣
- ንስር ለአደን እስከ 120 ኪሎሜትር አካሎ ይበራል፣
- ንስር መጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሆኖ ኃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በመምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣
- ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣
- ንስር ሲታመም ፀሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣
- ንስር 340° ማየት ይችላል። ከ360° በአንድ እይታ 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣
- ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ። ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል።
የመጀመሪያው ፤
ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል፣
ሁለተኛው ፤
አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ (መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፣
ሶስተኛው፤
ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።
1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።
ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።
፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።
፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡
ወዳጄ ሆይ:
ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ...ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡ... አትበል ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን
16/09/2022
አሁን አሁን ከምሰማው አባባልች አንዱ “fat ያላቸዉን ምግቦችን (ማለትም እንደ እንቁላል፣ ለዉዝ፣ አቩካዶ፣ ወተት(👀)...የመሳሰሉት) ከስፖርት በኋላ የምንመገብ ከሆነ የጡንቻን እድገት ላይ አሉታዊ ተጽኖ አለው” ሲባል ነው (maybe የኢትዮጵያ ፊትነስ ኢንደስትሪው ላይ ቅርብ ከሆናቹ እናንተም ሰምታችሁት ይሆናል)፣ ለዚም ምክንያት ተብሎ የሚቀርበው “fat ያላቸው ምግቦች digestive system slow ያረጉታል፣ ይህ ደሞ ፕሮቲን ወደ ጡንቻ እንዳይገባ ያረጋል በማለት ነው”፣
ግን ይህ ምን ያክል እውነት ነው?
የ2017 van Vliet S et al, ጥናት ላይ ሁለት ቡድኖች አምጥተው ልክ Exercise ሰርተው እንደጨረሱ, ቡድን አንድን egg whites (18 g protein እና 0 g fat) እንዲመገቡ አደረጎቸው፣ ቡድን ሁለትን ደሞ whole eggs (18 g protein እና 17 g fat) እንዲመገቡ አደረጉቸው፣ ከ1 ሳምንት እረፍት በኋላ ቡድኖቹን አቀያየሯቸው (ማለትም egg whites ይመገቡ የነበሩትን ወደ whole eggs፣ whole eggs ደሞ ወደ egg whites)፣
ተሳታፊዎቹ ምግቡን ከተመገቡ በኋላ ከ120 እና 300 ደቂቃ ላይ የprotein metabolic responseአቸዉን ተለኩ።
የጥናቱ ውጤት እደሚያሳየው whole eggs የተመገቡት ቡድኖች ከegg whites ከተመገቡት ቡድኖች አንጻር የበለጥ myofibrillar protein synthetic አሳይተዋል (see the graph)
የምር እደሚባለው fat ያለው ምግብ ከExercise በኋላ መመገብ digestive system slow አረጎ የprotein observation rate የሚቀንስ ቢሆን ኖሮ ተቃራኒ ውጤት እናይ ነበር!!
15/09/2022
ለሰውነት ግንባታ አጋዥ "ማሟያ" ጠቃሚ ምክሮች፡- 🔥
ያለ ምንም ጥርጣሬ በደንብ በመመገብ እና ክብደትን በማንሳት ብቻ ሰውነት መገንባት ይቻላል።
ነገር ግን ፣ የማደግ አቅምህን የበለጠ በብቃት ለማመቻቸት ፣ ለሰውነት አጋዥ ማሟያዎች አስፈላጊ ናቸው።
ተጨማሪ ምግብን በተመለከተ፣ በሳይንስ ከተመከሩት ጋር መቆየት አስፈላጊ ነው። ያንን ግምት ውስጥ በማስገባት ፣ በጣም የሚመከሩት 3 የሰውነት ግንባታ አጋዥ ማሟያዎች ተጨማሪ ምክሮች ከዚህ በታች አሉ።
1. የዓሳ ዘይት፡ ከደም ቧንቧ በሽታ ጀምሮ እስከ የተለያዩ በሰውነት ውስጥ ያሉ የካንሰር ዓይነቶች ላይ አዎንታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
2. ተጨማሪ ፕሮቲን መውሰድ በጡንቻዎች መጠን እና ጥንካሬ ላይ የበለጠ መሻሻልን ያመጣል።
3. የካርቦሃይድሬት ፈሳሽ መጠጦች መውሰድ ጠንክሮ ስፖርት ለሚሰሩ ሰዎች እና በሰውነታቸው ላይ ጡንቻ ለመጨመር ለሚፈልጉ ሰዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Assosa
Asosa
5220
